CURRENT

የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ35 በመቶ አደገ

By Admin

March 09, 2017

በተያዘው የበጀት ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገበው ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት በ35 በመቶ ማደጉን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ፐብሊክ ሪሌሽንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መኮንን ሀይሉ በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ የታየው ሰላማዊ ሁኔታ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋትና ወደ ግንባታ መግባት ለቀጥተኛ ኢንቨስትመንቱ መሻሻል ምክንያት መሆኑን አቶ መኮንን አስረድተዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ የአሜሪካ፣ አውሮፓና የእስያ ኩባንያዎችን ለመሳብ በማስቻሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታዋቂ ኩባንያዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ማደረግ መቻሉ ተገልጿል፡፡

እንደ እንቨስትመንት ኮሚሽን ገለጻ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ ሦስት የቻይና፣ ሁለት የህንድና የሌሎች አገሮች ኩባንያዎች በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የገቡ ሲሆንጥ ኪያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ የተባለው ኩባንያ በ945 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ አቅዷል፡፡

በተያያዘም ኢንዱስትሪያል ፓርኩ ውስጥ ቀደም ብለው ሥራ የጀመሩ ፋብሪካዎች ከመጋቢት ወር መጨረሻ በኋላ ምርታቸውን ወደ ውጭ ገበያ እንደሚያቀርቡ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ EBC