Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ግብፅ ወደ ስብስቡ መመለስ በምትችልበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ

0 544

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ግብፅ ወደ ናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ አባልነቷ ሙሉ ለሙሉ እንድትመለስ በሚያስችል ሁኔታ ላይ ትናንት በኢንቴቤ መክሯል።

ኢኒሼቲቩ ባወጣው መግለጫ ግብጽ ወንዙን በፍትሃዊነት እና እኩልነት ለመጠቀም በተፈረመው የትብብር ስምምነት ማዕቀፍ ላይ ካይሮን በተመለከተ የምክር ቤቱ ልዩ ኮሚቴ የሚወጣቸው ሪፖርቶችን አጥንታ ምላሽ ለመስጠት እንድትችል ተጨማሪ ጊዜ ስትጠይቅ ቆይታለች።

በመግለጫው መሰረት ግብጽ ወደ ሙሉ የኢኒሼቲቩ አባል ሀገርነት ለመመለስ የሚያስችላትን ሁኔታ ለማመቻቸት በኢንቴቤ በተካሄደው ስብሰባ ተሳትፋለች።

የትብብር ስምምነቱ ረቂቅ ላይ ሁሉም አባል ሀገራት የጋራ መስማማት እና ተሳትፎ አለማድረጋቸው በወደፊት የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ ችግር እንደሚፈጥር ነው ካይሮ የጠቀሰችው።

በስምምነት ሰነዱ አንቀፅ 14 ላይ የሰፈረው ሃሳብ የአሁናዊ እና የወደፊት የውሃ አጠቃቀም እና መብቶችን በአግባቡ አልተመለከተውም የሚል ጥያቄንም አንስታለች።

ምክርቤቱ በትናንቱ ስብሰባው ግብጽ ላነሳቻቸው ጥያቄዎች መልስ የሰጠ ሲሆን ግብፅ በበኩሏ ወደ ኢኒሼቲቭ አባል ሀገርነት ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ ጊዜ እንዲሰጣት ጠይቃለች፡፡

የኢንቴቤ ስምምነት በመባል የሚታወቀው የትብብር ስምምነት ማዕቀፉ ይፋ ከሆነበት 2010 ጀምሮ ግብፅ በናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ አልተሳተፈችም።

የትብብር ስምምነት ማዕቀፉ በስድስት የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት መፈረሙ ይታወቃል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy