English

የየካቲት አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ጭማሪ አሳየ

By Admin

March 08, 2017

የየካቲት አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ጭማሪ ማሳየቱን የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የተያዘው ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ ሰባት ነጥብ ዜሮ በመቶ ሆኗል።

የጥር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ስድስት ነጥብ አንድ በመቶ እንደነበር ያስታወሰው መግለጫው፤በየካቲት በዜሮ ነጥብ ስምንት በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አመልክቷል።በተያዘው ወር ከምግብ ክፍሎች አኳያ ከሩዝ በስተቀር በእህል ዋጋ ላይ ቅናሽ የታየ ሲሆን፤ በተለይም በቃሪያና ጎመን፣ በጥራጥሬ ፣በድንች በቆጮና ቡና ዋጋ ላይ ጭማሪ በመታየቱ የዋጋ ግሽበቱ ከፍ እንዲል ምክንያት መሆኑን አመልክቷል፡፡

የዚህ ዓመት የየካቲት ወር ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የስድስት ነጥብ ሁለት በመቶ ጭማሪ ማሳየቱንም አስታውሷል፡፡

ለዚህ ዋና ምክንያቶቹ በጫት፣ በልብስና በማገዶ እንጨት፣ በነዳጅ፣ በቤት እቃዎችና በቤት ማስጌጫዎች ላይ ጭማሪ በመታየቱ መሆኑን አመልክቷል፡፡