Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ

0 744

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌህ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ።ፕሬዚዳንት ጌሌህ ከነገ ጅምሮ ለሶስት ቀናት በኢትዮጵያ በሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት፥ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ስለማጠናከር ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ይመክራሉ።ፕሬዝዳንቱ ከፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ እና ሌሎች ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

በህዝብ ተወክዮች ምክር ቤት ተገኝተው ንግግር የሚያደርጉም ይሆናል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ፥ የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት የኢኮኖሚ ወህደት ለመፍጠር የተጀመረውን እንቅስቃሴ ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የጀመሩትን የኢኮኖሚ ውህደት እንቅስቃሴ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የጌሌህ ጉብኝት ፋይዳ እንዳለውም ገልፀዋል።ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የምጣኔ ሃብት እና አለም አቀፍ ግንኙነት ምሁራን፥ የኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ግንኙነት በሁለቱ ሀገራት መካከል የኢኮኖሚ ውህደት የመፍጠር ፍንጭ እየታየበት ያለ ብለውታል።

የሀገራቱ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ መሰረት ያለውና በህዝብ ለህዝብ መስተጋበር የተቆራኘ ስለመሆኑም ተናግረዋል።በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልማት ጥናት ትምህርት ክፍል መምህሩ ዶክተር ሰለሞን ፀሃይ፥ ሁለቱ ሀገራት የዜጎቻቸውን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፖለሲ መንደፋቸው አንስተዋል።

የግንኙነት መስመራቸውም የሁለቱን ሀገራት ብሄራዊ ጥቅም የሚያስከብር መሆን አለበት የሚል መሆኑን ጠቁመዋል።በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ቤት ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ሙሃሙድ አብዱላሂ ሁሴን በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ግንኙነት በምጣኔ ሀብት ብቻ ሳይሆን በማህበራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ውስጥም አስተማማኝ ሁኔታ ላይ ይገኛል ብለዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የምጣኔ ሀብት ትስስር ለማፋጠን እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አበረታች ነው የሚሉት የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ዶክተር ሰለሞን፥ ይህን አካሄድ ከማይቀለበስበት ደረጃ ለማድርስ በቀጣይም ይበልጥ ተጠናክረው ሊሰሩ ይግባል የሚሏቸው መስኮች አሉ።

ኢትዮጵያ ለጂቡቲ እያቀረበችው ያለው የኤሌክትሪክ ሀይል በርካታ የዚያች ሀገር ዜጎች ግንኙነቱ የህልውና ጉዳይ አድርገው እንዲወስዱት አድርጓችዋልም ነው ያሉት።

በዚህ መንገድ እየተጓዘ ያለውን የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በ1981 ገደማ አፍሪካዊያን አንድ የጋራ የኢኮኖሚ ውህደት ለመፍጠር የተስማሙበትን የአቡጃ ስምምነት እንዲሁም አሁን ላይ በአፍሪካ ህብረት እቅድ ወጥቶለት በየጊዜው ፍተሻ የሚካሄድበትን አጀንዳ በጥሩ ምሳሌነት ጠቅሰዋል።ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ከመሰረቱ ከአንድ ክፍል ዘመን በላይ አስቆጥረዋል።ኢትዮጵያ በጂቡቲ ቆንስላ ፅህፈት ቤቷን የከፈተችው በ1897 ነው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy