Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ድርጅቱ የሕዝብ ችግሮችን ለመፍታት ቁርጠኛ አቋም ይዞ እየሰራ ነው

0 883

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን / የሕዝብ ችግሮችን ለመፍታት የሚታዩ ተግዳሮቶችን በየደረጃው በመፈተሽ መፍትሔ ለመስጠት ቁርጠኛ አቋም በመያዝ እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡፡ከክልሉ ውጪ የሚገኙ የፊዴራልና የሌሎች ክልሎች የብአዴን አመራር አካላት የተጀመረውን ጥልቅ ተሃድሶ በማስቀጠልና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት ሂደት አባላቱ ተልዕኳቸውን የበለጠ አጠናክረው በሚቀጥሉበት ስልት ላይ ውይይት እያካሄዱ ናቸው።ሥልጠናው የድርጅቱን ጥልቅ ተሐድሶ በንድፈ ሐሳብ በሚደገፉ ርእሰ ጉዳዩች ላይ እንደሚያተኩር ነው የተገለፀው፡፡ከአማራ ክልል ውጭ የድርጅቱ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ እሸቴ አስፋው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት፤ ድርጅቱ እስካሁን የሕዝብ ችግሮችን የማዳመጥና የመፍታት ሥራዎችን በተግባር ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡በሥልጠናው ላይ በሚደረጉ ውይይቶች እስካሁን አመራሩ ያደረገውን ጥልቅ ተሐድሶ በንድፈ ሐሳብ ለማበልጸግ እንደሚያስችል አመልክተው፤ ይህም አባላቱ በተሻለ ቁመና ለአፈፃፀም በሚተጉበት አቅጣጫ ላይ እንደሚያተኩርም ተናግረዋል።ድርጅቱ በጥልቅ ተሐድሶ መድረኮች የተለዩትን አንገብጋቢ የሕዝብ ችግሮች መፍታት  መጀመሩን የጠቆሙት አቶ እሸቴ፤ ድርጅቱ ትምክህትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመዋጋት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።ድርጅቱ በጥልቅ ተሐድሶ የተነሱትን ችግሮችን የሚፈታበትን መንገድ አቅዶ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አመልክተው፤ አፈፃፀማቸውን በመከታተልና በመቆጣጠር ውጤታቸውን እየገመገመ እንደሚሔድም ተናግረዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy