Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ዶክተር መረራ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

0 686

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ዶክተር መረራ ጎዲና ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ።የተከሰሱበት የህግ አንቀጽ እስከ ሞት የሚደርስ ቅጣት ሊያሰጥ የሚችል በመሆኑ ነው የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገው።ተከሳሹ ዋስትና ህገመንግስታዊ መብት በመሆኑና ያለምንም ተጨባጭ ማሰረጃ ነው የታሰሩት በሚል ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ጠይቀው ነበር።ጠቅላይ አቃቤ ህግም የተጠረጠሩበት ወንጀል ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሃይል የመናድ ሙከራ በመሆኑ፣
በዋስትና ቢወጡ መረጃ ሊያሸሹ ይችላሉ በሚል እና ከሀገር ይወጣሉ በሚል ዋስትናው ውድቅ እንዲደረግ ጠይቋል።የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ግራ ቀኙን መርምሮ ተጠርጣሪው በተከሰሱበት የህግ አንቀፅ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ከ15 አመት በላይ፣ በእድሜ ልክ አልያም በሞት ሊያስቀጣ የሚችል በመሆኑ ዋስትናው ተቀባይነት የለውም ሲል ብይን ሰጥቷል።ዝርዝር የክስ መቃወሚያ ለመስማትም ለሚያዚያ 16 ቀን 2009 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy