በኢትዮጵያ አቆጣጠር 1960 ዎቹ አካባቢ ኢትዮጵያ አገራችን በብዙ ችግሮች በተወጠረችበት ወቅት ጃንሆይ ከልጅነታቸው ጀምሮ አብሮ አደጋቸው ከነበሩት ከራስ እምሩ ኃይለስላሴ ጋር በጃንሆይ ታላቁ ቤተመንግስት አብረው ተቀምጠው ሳለ የጃንሆይ ፊት፣ መልክ፣ አኳኋን አላማራቸውምና “ጃንሆይ ምን ሆነዋል በሰላም ነው? ፊትዎ ጠቁሯል ” አሏቸው። ጃንሆይም ” ጤንነት አይሰማንም አሞናል።” ሲሏቸውራስ እምሩ ኃይለስላሴም እንቅልፍ የነሳቸው ነገር የጃንሆይ ህመም ሳይሆን የአገራቸው የየዕለቱ ሁኔታ ነበርና ” ጃንሆይ እርስዎ ብቻ ሳይሆኑ ኢትዮጵያም እኮ አሟቷል።” ሲሉ ያገሪቷን ችግር ሕመም በጥበብ ነገሯቸው። ይባላል።