Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ግድቡ የሃገራቱን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው – የሱዳን የፓርላማ አባላት

0 402

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሁለቱን ሃገራት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን የሱዳን የፓርላማ አባላት ገለጹ።

የሃገሪቱ የፓርላማ አባላት ከኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ ጋር ትናንት ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በአባይ ላይ የሚገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፥ የተፋሰሱን ሃገራት ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ እንደሚገነባ አንስተዋል።

ግድቡን የመጎብኘት አላማ እንዳላቸው የጠቀሱት አባላቱ፥ ጉብኝቱ የሁለቱን ሃገራት የቆየ ወዳጅነት እና የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ ይረዳል ብለዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የምታደርገውን ትብብር አጠናክራ መቀጠል ትፈልጋለች ነው ያሉት።

የሃገራቱን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከርም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሱዳን ፓርላማ ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈ ግድቡ የሱዳንንም ሆነ የግብጽን የውሃ ድርሻ በማሳነስ ጉዳት የማድረስ አላማ እንደሌለው ተናግረዋል።

በውይይቱ ሁለቱ ሃገራት የጋራ በሆኑ የሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

አባላቱ በተለይም የሃገራቱን የፓርላማ ግንኙነት ማሳደግና ማጠናከር በሚቻልባቸው አግባቦች ላይም መክረዋል።

ሱዳንና ኢትዮጵያ ጠንካራ ወዳጅነት ያላቸው ጎረቤታሞች ሲሆኑ፥ የሃገራቱ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድንም በየአመቱ በመገናኘት እንደሚወያይ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ሱዳን ትሪቢዩን

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy