CURRENT

ጠ/ሚ ኃይለማርያም በዘመናዊ አሠራር ሃብት ያፈሩ 291 አርሶና ከፊል አርብቶ አደሮችን ነገ ይሸልማሉ

By Admin

March 11, 2017

ዘመናዊ አሰራርና ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ሃብት ያፈሩ 291 አርሶ እና ከፊል አርብቶ አደሮች ነገ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማሪያም ደሳለኝ ይሸለማሉ።

በግብርና ዘርፍ ተሰማርተው ሃብት በማፍራት ወደ ኢንቨስትመንት የተሸጋገሩ አርሶ አደሮችም ይመረቃሉ።

የሚመረቁት አርሶ አደሮች ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ሃብት በማፍራት በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ተሰማርተው ለሌሎች የሥራ እድል የፈጠሩ ናቸው።

በግንባር ቀደምትነት የሚሸለሙት አርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች፥ ሃብት እንዲያፈሩ ከፍተኛ እገዛ ያደረጉ የግብርና ባለሙያዎችና አመራሮችም በሽልማቱ ተካተዋል።

የግብርና ምርምር ማዕከላት፣ የህብረት ስራ ማህበራት፣ ባለሃብቶችን ጨምሮ 557 በግብርናው ዘርፍ አስተዋፅኦ ያላቸው ባለድርሻዎች ተሸላሚ ይሆናሉ።

እርሻን በማዘመን የኢንዱስትሪ ሽግግር መሰረት እንጠቃል በሚል መሪ ቃል ስምንተኛው ሀገርአቀፍ የአርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች ፌስቲቫል በአዳማ እየተካሄደ ይገኛል ።