Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ጣሊያን ለኢትዮጵያ የ500 ሺህ ዩሮ ድጋፍ አደረገች

0 521

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ጣሊያን ለኢትዮጵያ ለግል ዘርፍ ልማት የሚውል የ500 ሺህ ዩሮ ድጋፍ አደረገች።

ድጋፉ በዓለም ባንክ የዓለም ዓቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የልማት መርሃ ግብሮች መካከል አንዱ ለሆነው “ለግል ዘርፉ ልማት መርሃ ግብር” ማስፈጸሚያ የሚውል ነው።

ድጋፉ የተደረገው ከተለያዩ ለጋሽ አካላት ገንዘብ በማሰባሰብ ለታዳጊ አገሮች የግል ዘርፍ ድጋፍ በሚሰጠው “በመልቲ ዶነር ኢንሸቲቭ ፎር ፕራቬት ሴክተር ደቨሎፕመንት” በተሰኘው የጋራ ትብብር ማዕቀፍ በኩል ነው።

የድጋፍ ስምምነቱ ፊርማ ስነ ስርዓትም ከሶስቱም ወገን ተወካዮች በተገኙበት በጣሊያን ኤምባሲ ዛሬ ተካሂዷል።

ስምምነቱ ለግል ዘርፉ እድገት በተለይም ለአነስተኛና መካከለኛ የማምረቻ ኢንተርፕራይዞች ልማት የሚውል ነው።

የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የሰሃራ በታች የልማት ትብብር ኃላፊ ኢቫ ባኮኒ እንደገለጹት፤ ድጋፉ ያስፈለገው ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለው ተከታታይ እድገት ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ የማምረቻውን ዘርፍ ለማጠናከር ነው።

ለወጣቶች ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥሩ አነስተኛና መካከለኛ የማምረቻ ዘርፎች እንዲዳብሩ የአቅም ግንባታ ስራዎች ለመስራት እንደሚያግዝ ነው የተናገሩት።

በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ጁሴቴ ማስትሬት በበኩላቸው፤ የጣሊያን መንግስት ለኢትዮጵያ የሚያደርገው የፋይናንስ ድጋፍ ከጊዜ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።

ጣሊያን በንጹህ መጠጥ ውሃ፣ በትምህርትና በጤና መሰረተ ልማቶች ከምታደርገው ድጋፍ በተጨማሪ አገሪቷ ወደ ኢንዱስትሪ ለምታደርገው ሽግግር የግሉ ዘርፉ እንዲዳብር ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥልም ነው የተናገሩት።

የጣሊያን መንግስት በዓለም ዓቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በኩል ለኢትዮጵያ ያደረገችው ድጋፍ የአሁኑን ጨምሮ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ዩሮ መድረሱን ኢዜአ ዘግቧል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy