Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ጥልቅ ተሃድሶው በአመለካከትና በተግባር የታዩ ችግሮችን አርሟል–ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም

0 481

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በጥልቀት የመታደስ ሂደቱ በአመለካከትና በተግባር የታዩ ህፀፆችን እያስተካከለ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን ያለፉት 6 ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ ጥልቅ ተሃድሶው በአመለካከት የታዩ ዝንባሌዎችን በማስተካከልና በተግባር የታዩ ስህተቶችንና ብልሹ አሰራሮችን በማረም ውጤት አስገኝቷል ብለዋል፡፡

በመሪው ድርጅት ኢህአዴግ የተለኮሰው የጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ በቀጣይ የሃገሪቱን ፈጣን እድገትና የተሃድሶ ጉዞ ለማስቀጠል መግባባት የተደረሰበትና ወደ ተግባርም ለመግባት ምቹ ሁኔታ የተፈጠረበት መሆኑን አንስተዋል፡፡

ሂደቱ በአንድ ጊዜ ተጀምሮ የሚያልቅ ሳይሆን በሂደት በስራ ውስጥም ሆኖ እየታደሱ የሚሄድበት አሰራር ስለሚኖር ገና ተጀመረ እንጅ አላለቀም ብለዋል፡፡መንግስት ቀጥተኛ የህዝብ ተሳትፎን ማጎልበትና ከአጋር አካላት በተለይም ከሲቪክ ማህበራት ጋር ተቀናጅቶ መስራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት በተሃድሶው ከተለዩት ውስጥ እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል፡፡

ዲሞክራሲያዊ ስርዓቱ ይበልጥ እንዲጎለብት ከሚል መነሻም በፓርቲዎች መካከል ውይይትና ድርድር የማካሄድ ስራ ተጀምሯል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚያግባቡ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስራትና በሚያለያዩ ጉዳዮች ደግሞ ዳኝነቱን ለህዝብ በመተው ተቀራርቦ ይሰራል ብለዋል፡፡

እናም የባለፉት 15 ዓመታት የጉዞ ሂደትን በመገምገም የጀመረው የጥልቅ ተሃድሶ ጅምር ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ባካተተና ባሳተፈ መልኩ ይበልጥ እየተጠናከረ ይሄዳልም ነው ያሉት፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy