ጥጥና ክላሽ የጫነች አይሱዙ መኪና የተከዜን ድንበር ተሻግራ ወደ ኤርትራ በመግባት ላይ እንዳለች በቁጥጥር ስር ዋለች።
በትናንትናው እለት ማለትም 20/07/2009 ዓ.ም ምሽት 2 ሰዓት ላይ ጥጥና ቁጥራቸው 350 የሚደርስ ክላሽ ጭና የተከዜን ድንበር በመሻገር ወደ ኤርትራ በመግባት ላይ የነበረች አይሱዙ መኪና በአካባቢው የፀጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር ውላለች። ለመግባት የሞከረች መኪና በቁጥጥር ስር መዋልዋን የምዕራባዊ ትግራይ ዞን ፀጥታ ፅ/ቤት አስታውቋል።
i አይሱዙ መኪናዋ በቁጥጥር ስር እንድትውል በማድረጉ ረገድ ከመከላከያ ሰራዊታችን እና ከአካባቢው የፀጥታ ሀይሎች በተጨማሪ በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ላይ ፍየል በመጠበቅ ላይ የነበሩ ኤርትራውያን ወጣቶች ተባባሪ እንደነበሩ የምዕራባዊ ትግራይ ዞን ፀጥታ ፅ/ቤት ጨምሮ ገልጿል።