Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ፓርቲዎቹ በድርድሩ አጀንዳ ዓላማ ዙሪያ ስምምነት ላይ ደረሱ

0 402

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢህአዴግን ጨምሮ 22 አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚደራደሩበት አጀንዳ ዓላማ ዙሪያ ስምምነት ላይ ደረሱ።ኢህአዴግ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ለመደራደር ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳበዚህም 21 አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ከኢህአዴግ ጋር እየተወያዩ ይገኛሉ።ዛሬ 22ቱ አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች “የምንደራደረው ከዚህ ግብ ለመድረስ ነው” ብለው ባነሱት ጉዳይ ላይ ተወያይተው ስምምነት ላይ ደርሰዋል።በዚሁ መሰረት “በድርድር ወቅት የሚነሱ የተለያዩ ሃሳቦችን እንደ ግብዓት በመጠቀም መሰረታዊ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸውን የሚሻሻሉ ህጎችን ማሻሻል የአፈፃፀም ጉድለቶችን ማስተካከል” በሚል ሀሳብ ላይ ተስማምተዋል።ቀደም ብሎ በደረሱት መግባባት መሰረት ውይይቱን የመሩት የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ  “በአገራችን የፖለቲካ ምህዳርና የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ያጋጠሙ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት መፍትሄ እንዲሰጥ ማስቻል” የሚለውን ጨምሮ በአምስት የድርድር ዓላማዎች ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።”ሥልጣን በምርጫ ሥርዓት ብቻ አሸናፊ ለሆነው የፖለቲካ ፓርቲ  የሚተላለፍበትን ወሳኝ ምዕራፍ በሀቀኝነትና በቁርጠኝነት ተነስተን እውን እንዲሆን የድርሻችንን ለመወጣት ነው” የሚለው ሃሳብ የድርድሩ አጀንዳ እንዲሆን ተወስኗል።ፓርቲዎቹ ከዚህ በፊት ባደረጉት ስምምነት መሰረት የዛሬው ውይይት በኢህአዴግ የተመራ ሲሆን፤ መገናኛ ብዙሃንም በስብሰባው እንዲገኙ ተደርጓል።የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው የጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ ማጠቃለያ ላይ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል በአገሪቷ በህጋዊ መንገድ ከተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት፣ ክርክርና ድርድር ማድረግ የሚለው ይገኝበታል።ፓርቲዎቹ በቀሪዎቹ ጉዳዮች ላይ ለመወያየትና ረቂቅ ደንቡን ለማፅደቅ ለየካቲት 30 ቀን 2009 ዓ.ም ቀነ ቀጠሮ ይዘዋል።

 

 

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy