Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስደተኞችን የተመለከተ አዲስ ውሳኔ አሳለፉ

0 286

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዚዳንታዊ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ስደተኞችን የተመለከተ አዲስ ውሳኔ አሳለፉ።

አዲሱ ስደተኞችን የተመለከተ ውሳኔ የስድስት ሀገራት ዜጎች ለ90 ቀናት አሜሪካ እንዳይገቡ የሚከለክል ነው።

ኢራቅ ከዚህ ቀደም በፕሬዚዳንቱ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እገዳ ተጥሎባቸው ከነበሩ ሀገራት ውስጥ ወጥታለች። ህጋዊ ቪዛ የያዙ ኢራቃውያን አሜሪካ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል።

የጉዞ ትርምስን ለመቀነስም ከማርች 16 ጀምሮ ለ120 ቀናት ማንኛውም ስደተኛ አሜሪካ እንዳይገባ ተከልክሏል በአዲሱ ውሳኔ።

የኢራን፣ ሊቢያ፣ ሶሪያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና የመን ዜጎች በ90 ቀናት ውስጥ አሜሪካ እንዳይገቡ የጉዞ እገዳ ተጥሎባቸዋል።

ይሁን እንጂ በሀገሪቱ ስቴት ዲፓርትመንት ተቀባይነት ያገኙ ስደተኞች አሜሪካ እንዲገቡ እንደሚፈቀድላቸው የተገለፀ ሲሆን፥ በያዝነው የፈረንጆቹ አመት ወደ ሀገሪቱ እንዲገቡ የሚፈቀድላቸው ስደተኞች ቁጥር ከ50 ሺህ እንደማይበልጥ ተመላክቷል።

በሀገሪቱ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ከላይ የተጠቀሱት ስድስት ሀገራት ዜጎች ይህ አዲሱ የትራምፕ ውሳኔ አይመለከታቸውም ተብሏል።

ትራምፕ ወደ ስልጣን በመጡ ሰሞን ስደተኞችን አስመልክቶ ያሳለፉት ውሳኔ በአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት ውድቅ መደረጉ በአውሮፕላን ማረፊያዎች አካባቢ ውዝግብ መፍጠሩ እና ለተለያዩ የተቃውሞ ሰልፎች ምክንያት መሆኑ የሚታወስ ነው። FBC

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy