Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሙሉ ለሙሉ ግንባታቸው የተጠናቀቁ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ በይፋ ተመርቀዋል።

0 829

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሙሉ ለሙሉ ግንባታቸው የተጠናቀቁ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ በይፋ ተመርቀዋል።

በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም በሰንጋተራ ሳይት የተገነቡትን ቤቶች ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ ነው በይፋ የመረቁት።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባደረሰው መረጃ ከአዳዲሶቹ በተጨማሪ ባለፈው ሀምሌ ወር ላይ እጣ የወጣባቸው ከ39 ሺህ በላይ የ20/80 እና የ10/90 ቤቶችም በዛሬው እለት ተመርቀዋል።

የመዲናዋ የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ በመስከረም ወር 2009 በሰንጋተራና ክራውን ሳይቶች ግንባታቸው የተጠናቀቁ የ40/60 ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን መግለፁ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ቤቶቹ እስካሁን እጣ አልወጣባቸው።

በሰንጋተራና ክራውን ሳይቶች ግንባታቸው ተጠናቆ ዛሬ የተመረቁት 1 ሺህ 292 የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በቅርቡ እጣ ይወጣባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በባንክ በኩል እጣ በቅርቡ እጣ ይወጣባቸዋል የተባለ ሲሆን፥ በእጣው ቅድሚያ ሙሉ ለሙሉ ከፍለው ያጠናቀቁ ዜጎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር በ2009 በጀት ዓመት 18 ሺህ 496 የ40/60 ፕሮግራም ቤቶችን እንደሚያስተላልፍ ቢገልፅም እስካሁን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ አልወጣም።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy