Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

121ኛው የአድዋ ድል በዓል ነገ በመላ ሀገሪቱ ይከበራል

0 663

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

121ኛው የአድዋ ድል በዓል ነገ በመላ ሀገሪቱ ይከበራል።

በዓሉ የአድዋ ጦርነት በተከናወነበት የአድዋ ተራሮች የሚከበር ሲሆን በመላ ሀገሪቱም በተለያዩ ስነ ስርአቶች ይከበራል።

የአድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ባልተመቸ ሁኔታ ውስጥ ሆነው እንኳን ሀገራቸውን ለጠላት አሳልፈው የማይስጡ ህዝቦች መሆናቸው ማረጋገጫ ማህተም ነው ብለዋል አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ።

አፈ ጉባኤው ድሉ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በኖረበት የዘመን ለሀገሩ አንዳች ነገር አበርክቶ ማለፍ እንዳለበት የሚያስተምር መሆኑን ተናግረዋል።

በአድዋ ጦርነት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከዳር እሰከ ዳር ተሰልፎ የጣሊያንን ወራሪ ሀይል ተዋግቷል ያሉት አቶ አባዱላ፥ እያንዳንዱ ትውልድ የየራሱ የቤት ስራ አለው ብለዋል።

ኢትዮጵያዊ እየተጨቆነ እንኳን ሀገሩን አሳልፎ አይሰጥም፤ በረጅም ጊዜ የተፈጠረ ጠንካራ ትስስርም አለው ነው ያሉት።

ሁሉም ዜጋ በእኩልነት እና በመከባበር የሚኖርበትን ሁኔታ ለመፍጠር መታገል ተገቢ መሆኑንም አንስተዋል።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም በበኩላቸው፥ አድዋ የመላ አፍሪካውያንና የጭቁን ህዝቦች ድል በመሆኑ ድሉን ከማክበር ባለፈ ማስታወሻ ሊሆኑ የሚችሉ ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል።

ዶክተር ሂሩት አያይዘውም የአድዋን ድል ዘላለማዊ ለማድረግና የጥናትና ምርምር ስራዎች እንዲሰሩበት የሚያስችሉ ተቋማት እንደሚገነቡ አስታውቀዋል።

በመሆኑም በአድዋ ተራሮች ሙዚዬምን ጨምሮ ሌሎች ለቱሪስት መስህብነት የሚውሉ ተቋማት ይገነባሉ ነው ያሉት።

የአሁኑ ትውልድም ይህን አኩሪ ተግባር ማስቀጠል እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በዓሉ የሚበርባት የአድዋ ከተማም በዓሉን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ተዘጋጅታለች።

የከተማዋ ከንቲባ አቶ ክንደያ አጽብሀ፥ በዓሉን ለማክበር በከተማው ሰፊ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

በዓሉ የጥቁር ህዝብ እንደመሆኑ ከዚህም የቱሪዝም ተጠቃሚነትን ለማምጣት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

የፓን አፍሪካ የምርምር ማዕከልን እና ማህበረሰቡን ከኢኮ ቱሪዝም ተጠቃሚ ለማድረግ የሚሰራ ይሆናልም ነው ያሉት።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy