Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

21ዱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰባተኛ የድርድር ቅድመ ውይይታቸውን ነገ ያካሂዳሉ

0 391

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከኢህአዴግ ጋር የድርድር ቅድመ ውይይት እያካሄዱ ያሉት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠንካራ አንድነት መፍጠር ተስኗቸዋል።

ባለፉት ሁለት ወራት በተካሄዱ ስድስት ውይይቶች የተሳተፉት፥ 22 የፖለቲካ ፓርቲዎች መግባባት ላይ ሳይደርሱ ሰባተኛውን ድርድር ነገ ያደርጋሉ።

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ለድርድር እና ክርክር ወይም ለድርድር ብቻ በምን መልክ እንቅረብ በሚለው ሃሳብ ላይ መስማማት አልቻሉም።

መኢአድ፣ ሰማያዊ ፓርቲ እና ኢዴፓን ጨምሮ ስድስት ፓርቲዎችን የያዘው ስብስብ፥ ከየፓርቲዎቹ በተውጣጣ ተወካይ ድርድሩ እንዲካሄድ ይፈልጋል።

አንድነት፣ ቅንጅት፣ አትፓን ጨምሮ ሌሎች ከስድስት በላይ ፓርቲዎችን የያዘው ስብስብ ደግሞ፥ ሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጥታ ለድርድር ይሰየሙ የሚል አቋም አለው።

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንደነት መድረክ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር በየነ ጰጥሮስ በበኩላቸው፥ መድረክ እንዲህ ያለ የሸንጎ ድርድር እንደማይፈልግ ይናገራሉ።

ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ፓርቲዎቹ በፈለጉት መንገድ ቢመጡ ለማስተናገድ ዝግጁ ነኝ በማለት ሶስቱን ሃሳብ ተቀብሏል።

ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ለድርድር እንዴት እንቅረብ በሚለው ጉዳይ ላይ ለመወሰን ያደረጉት ስብሰባ ያለ ውጤት ከተበተነና መድረክም ድርድሩ በእኔ እና በኢህአዴግ መካካል መካሄድ አለበት የሚል ሃሳብ ካቀረበ በኋላ በፓርቲዎቹ መካካል ያለው ልዩነት ወደ መወቃቀስ ተሸጋግሯል።

ፓርቲዎቹም የመድረክን አካሄድ የሌሎቹን ተሳትፎ የሚገድብና አግላይ ነው በማለት ተችተውታል።

መድረክም ፓርቲዎቹን ወክየ ከኢህአዴግ ጋር መደራደር አለብኝ በማለቱ ልዩነታቸውን ማስታረቅ አልቻሉም።
ፓርዎቹ ዛሬም እንዴት ከኢህአዴግ ጋር እንደራደር በሚለው ጉዳይ ላይ የተለያየ ሃሳብን የያዙ ሲሆን፥ ከመድረክ በቀር ሌሎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያለ ሶስተኛ ወገን ድርድሩ አይካሄድም የሚል አቋም አላቸው።

በነገው እለት በሚኖራቸው ሰባተኛ ዙር ውይይትም ኢህአዴግ የያዘው ስለ አደራዳሪ ጉዳይ፣ መድረክ ስለ ያዘው የተናጥል ድርድር ሃሳብ የሚሰጠው ምላሽ እና ሌሎቹ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አግላይ ስለሚሉት የመድረክ አካሄድ ይዘው የሚቀርቡት አቋም ይጠበቃል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy