Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

22ቱ ፓርቲዎች በአደራዳሪ ጉዳይ መግባባት ላይ ሳይደርሱ በቀጠሮ ተለያዩ

0 324

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

22 ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በ7ኛ ዙር ውይይታቸው በአደራዳሪ ጉዳይ ላይ ሁለት የተለያየ አቋም ይዘው ተከራክረዋል።

በዚህ ውይይትም መግባባት ላይ መድረስ አልቻሉም።

በ6ኛው ዙር ውይይት ሶስተኛ ወገን አደራዳሪ ያስፈልጋል የሚል አቋም ይዘው የነበሩ ፓርቲዎች ዛሬ አቋማቸውን ቀይረው ቀርበዋል።

ፓርቲዎቹ አንድነት፣ ቅንጅት፣ ኢትፓ፣ ኢዴአን፣ ኢዴህ እና ወህዴፓ ናቸው።

የመላው ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ከአሁን በፊት በያዘው አቋሙ በመፅናት ሶስተኛ ወገን አደራዳሪ አያስፈልግም የሚለውን አቋሙን ደግሞ ገልጿል።

ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በበኩሉ ድርድሩ በፓርቲዎች በዙር ወይም ከፓርቲዎች በሚመረጡ ይመራ የሚለው የመጨረሻ አቋሙ መሆኑን አስታውቋል።

በሌላ በኩል ኢዴፓ፣ ሰማያዊ ፓርቲ፣ ኢራፓን የያዘው የስድስት ፓርቲዎች ስብስብ ያለ ሶስተኛ ወገን ድርድር አናካሂድም በሚለው አቋማቸው እንደፀኑ ናቸው።

የገዳ ስርአት አራማጅ ፓርቲ የሶስተኛ ወገን አደራዳሪ መኖር አለመኖር አጀንዳዎችን መሰረት አድርጎ ይወሰን፤ እንደ አጀንዳዎቹ በሶስተኛ ወገን አልያም በፓርቲዎች በዙር ልንደራደር እንችላለን ብሏል።

የሶስተኛ ወገን አደራዳሪ አያስፈልግም ያሉት ፓርቲዎች ሰላማዊ በሆነች ሀገር በሰላማዊ ፓርቲዎች መካከልየሚደረግ ድርድር ሰላምን ባጡ ሀገራት እንደሚደረገው አይነት በሶስተኛ ወገን የሚደረግ ድርድር አያስፈልግም፤ ማንም ሰው ከፖለቲካ አስተሳሰብ ነፃ እና ገለልተኛ ይሆናል ብለን ስለማናስብ ገለልተኛ እና ነፃ አደራዳሪ የሚለውን አንቀበለውም፤ አደራዳሪው መድረክ ከመምራት ባሻገር ሌላ ሚና ስለማይኖረው አያስፈልገንም የሚል ምክንያት አቅርበዋል።

ሶስተኛ ወገን አደራዳሪ ያስፈልጋል የሚሉት ስምንት ፓርቲዎች ደግሞ ነፃ እና ገለልተኛ ስንል የፓርቲ አባል ያልሆኑ ግለሰቦች ማለታችን ነው፤ ስለዚህ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ሊያደራድሩን ይገባል፤ ኢህአዴግን ስለማናምነው ሶስተኛ ወገን አደራዳሪ ወገን እንዲኖር እንፈልጋለን የሚል ምክንያት አቅርበዋል።

ኢህአዴግ በበኩሉ ከአሁን ቀደም ያለ ሶስተኛ ወገን አደራዳሪ በፓርቲዎች ብቻ በተደረጉ ድርድሮች የምርጫ ህጎች መሻሻላቸውን በማንሳት አንድ ግለሰብ የፓርቲ አባል አይደለም ማለት የሆነ አስተሳሰብ ደጋፊ ነው ማለት ስላልሆነ ገለልተኛ እና ነጻ አደራዳሪ የሚለውን ሀሳብ አልቀበልም ብሏል።

ፓርቲዎቹ በዛሬው ውይይት መግባባት ላይ ባለመድረሳቸው በሚያዚያ 2 2009 ዓ.ም ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘው ተለያይተዋል። FBC

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy