Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

3 ሺህ 400 የ10/90 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በአነስተኛ ኪራይ እንዲተላለፉ ተወሰነ

0 546

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ግንባታቸው ተጠናቆ እጣ ያልወጣባቸው 3 ሺህ 400 የ10/90 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች በአነስተኛ ኪራይ እንዲተላለፉ ተወሰነ።በቅርቡም በካቢኔው ፀድቆ ወደ ተግባር ይገባል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እንዳለው፥ እጣ ወጥቶባቸው ርክክብ ያልተፈፀመባቸው ሌሎች 3 ሺህ 200 ቤቶችንም ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው።

የቢሮ ሀላፊ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ቢሮው በቂሊንጦ ሳይት በአንድ አከባቢ የሚገኙትን ቤቶች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ለመንግስት ሰራተኞች በአነስተኛ ዋጋ ለማከራየት ከውሳኔ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።

ውሉን ያላቋረጠ የ10/90 ቤቶች ተመዝጋቢ መቶ በመቶ የቤት ተጣቃሚ መሆኑን ያስታወሱት ሀላፊው፥ አሁንም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በሂደቱ ያልተካተተ ነዋሪ ካለ አሳውቆ ከተረጋገጠ ቤቱ የሚሰጠው ይሆናል ብለዋል።

ከዚህ ውጪ ቤቶቹን በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ መሰረት ለኪራይ ዝግጁ የማድረግና ዝርዝር ጉዳዩን በሚመለከት ለአስተዳደሩ ካቢኔ ቀርቦ ውሳኔ ይሰጥበታል ነው ያሉት።

ካቢኔው በቤቶቹ ጉዳይ ላይ ውሳኔ እንዳሳለፈ መስፈርቱን የሚያሟሉ ነዋሪዎች ተለይተው በዝቅተኛ ዋጋ ለማከራየት እጣ እንዲወጣባቸው ይደረጋል።

በሌላ በኩል እጣ ከወጣባቸው ከ30 ሺህ በላይ ቤቶች ቁልፉን የተረከቡት 27 ሺህ ባለእድለኞች ናቸው።

እነዚህ ነዋሪዎች ከተረከቧቸው ቤቶች በተጓዳኝ እጣ ወጥቶባቸውና ባለእድለኞቹ ተለይተው ቁልፍ ያልተወሰደባቸው 3 ሺ 225 ያህል ቤቶች አሉ።

የእነዚህ ቤቶች ባለእድለኞች አሳማኝ ምክንያት ካላቸው የመጨረሻ እድል እንዲሰጣቸው የሚደረግ ሲሆን፥ ይህን ተከትሎ ግን ቤቶቹ በኪራይ መልክ ወይም መልሶ እጣ እንዲወጣባቸው የሚል ውሳኔ ተሰጥቶት ወደ ተግባር ይገባል ነው ያሉት አቶ ይድነቃቸው። FBC

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy