Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

“ምድረ ቀደምት” የሚለው መለያ የኢትየጵያን የሰው ዘር መገኛነት ይገልጻል–የአለም የቱሪዝም ድርጅት ዋና ጸሃፊ

0 1,079

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

“ምድረ ቀደምት” የሚለው አዲሱ የኢትየጵያ የቱሪዝም መለያ የሀገሪቱን ጥንታዊነትና የሰው ዘር መገኛነት የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ በተባበሩት መንግስታት የአለም የቱሪዝም ድርጅት ዋና ጸሃፊ ዶክተር ታሌብ ሪፋይ ተናገሩ።

የ59ኛው የአፍሪካ ቱሪዝም ኮሚሽን ጉባኤ አባላት በአለም ቅርስነት የተመዘገበውን የፋሲል አብያተ መንግስታትን ጨምሮ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የቱሪዝም ቅርሶችን ዛሬ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት ዋና ጸሃፊው ዶክተር ታሌብ ሪፋይ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት “ኢትዮጵያ በርካታ ብሄር ብሄር ብሄረሰቦችና ሃይማኖቶች ተከባብረውና ተፈቃቅረው የሚኖሩባት ሀገር ነች” ብለዋል።

“ኢትዮጵያ ብዝሃነትን የተቀበለችና ያከበረች ሀገር ነች” ያሉት ዋና ጸሃፊው ኩሩና እንግዳ ተቀባይ ህዝብ እንዳላትም ተናግረዋል።

“አዲሱ የቱሪዝም መለያ መላው የአለም ህዝብ የዘር ግንዱ ምንጭ ኢትዮጵያ መሆንዋን ይበልጥ እንዲያውቅና እንዲገነዘብ ብሎም የቀደምት ቅደመ አያቶቹን ሀገር እንዲጎበኝ የሚያነሳሳ ነው” ብለዋል።

በጎንደር ከተማ የጎበኘኋቸው ቅርሶችም ኢትዮጵያ የጥንታዊ ገናና ስልጣኔና የጥበብ ባለቤት እንደነበረች የሚያመላክቱ የታሪክ አሻራ ማረጋገጫ መሆናቸውን ተገንዝቤአለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ብትሆንም ሰላሟ የተረጋገጠ ህዝቡ ከቦታ ቦታ ያለምንም ስጋት ለስራም ሆነ ለመዝናናት ሲንቀሳቀስ በማየት ማረጋገጣቸውንም ገልጸዋል።

የድርጅቱ ምክትል ዳይሬክተር ዙ ቪንዝ ሆን በበኩላቸው ወደ ኢትዮጵያ የመጀመሪያቸው መሆኑን ገልጸው “ሃገሪቱ ውብና ማራኪ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ባለቤት በመሆኗ ከቱሪዝም ሀብቷ ይበልጥ ለመጠቀም ሰፊ የማስተዋወቅ ስራ ማድረግ አለባት” ብለዋል፡፡

“እኔ የቻይና ዜጋ እንደመሆኔ በርካታ ቻይናውያን ሀገር የመጎብኘት ልምድና ፍላጎት አላቸው ከአውሮፓ ይልቅ ሰፊ የበረራ መስመሮች ወደ አፍሪካ አሉ ይህን አመቺ ሁኔታ መጠቀም አስፈላጊ ተገቢ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እንደ የአለም ቱሪዝም ድርጅት ምክትል ዳይሬክተርነታቸው አፍሪካ ብሎም ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ድርጅቱ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

የአንጎላ የቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ፕሮሞሽን ዳይሬክተር ሚስተር አንጌሎ ጂሶዴ በበኩላቸው “ኢትዮጵያ የበርካታ ጥንታዊና ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት መሆንዋን ዛሬ በጎበኘሁት የፋሲል ቤተ መንግስት ማረጋገጭ ችያለሁ” ብለዋል።

“የአፍሪካ ሀገሮች እርስ በእርስ በቱሪዝም ዘርፍ ግንኙነታቸውን ማጠናከር ይገባቸዋል”  በማለት እሳቸውም ሃገራቸው ሲመለሱ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብቶች በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለማስተዋወቅ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በዋና ጸሃፊው የተመራው የአፍሪካ የቱሪዝም ኮሚሽን ጉባኤ አባላት በጎንደር ከተማ የሚገኘውን የአጼ ፋሲል አብያተ-መንግስትን ጨምሮ የደብረ ብርሃን ስላሴ ጥንታዊ ቤተክርስቲያን፤ የጎንደር ዩንቨርሲቲ የባህል ማእከልን የጎበኙ ሲሆን በፋሲለደስ መዋኛም የመታሰቢያ ችግኝ ተክለዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy