Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የተሳተፈው ግለሰብ በገንዘብና በእስራት ተቀጣ

0 734

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያውያንን ለስራ ወደ ውጭ ሀገር ለመላክ የሚያስችል ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው ሁለት ግለሰቦችን ሳውዲአረቢያ እልካችኋለሁ  በሚል ካልተያዘ ግብረአበሩ የመጡለትን ግለሰቦች ሲያጓጉዝ  የተደረሰበት ግለሰብ በእስራትና በገንዘብ ተቀጥቷል፡፡

ተስፋዬ ሃይሉ ሃሽ በኢፌዴሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 598/1/ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በላይ አባዲና ወልደሩፋኤል ተሰፋዬ የተባሉትን ግለሰቦች ለስራ ወደ ሳውዲአረቢያ ለመላክ  ካልተያዘ ግብረአበሩ ተቀብሎ  ሲያጓጉዛቸው በፖሊስ ተደርሶበት ነው ቅጣቱ የተላለፈበት፡፡

ለጊዜው ያልተያዘው የተከሳሽ ግብረአበር ተበዳዮችን ለስራ ወደ ሳውዲአረቢያ እልካችኋለሁ በሚል ለጊዜው መጓጓዣ የሚሆን ከእያንዳንዳቸው 600 ብር ተቀብሎ ተበዳዮችን ከአፋር ክልል ሎጊያ ከተማ ወደ ዲቼቶ ከተማ ይልካቸዋል፡፡

ተከሳሽ ተበዳዮችን ተቀብሎ ወደ ሳውዲአረቢያ ለሚያሻግራቸው ግብረአበሩ ለማስረከብ በባጃጅ ይዟቸው በመብረር ላይ ሳለ  ነበር ከፖሊስ እጅ ገባው፡፡

ፖሊስ በተከሳሹ ላይ አስፈላጊውን መረጃ ካጠናቀረ በኋላ ደግሞ ጉዳዩን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት መራው፡፡

ምድብ ችሎቱም የቀረቡትን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች መርምሮ መጋቢት 25/2009 ተከሳሹ ላይ የሰባት ዓመት ከስምንት ወር ጽኑ እስራትና የሁለት ሺህ ብር ቅጣት ወስኖበታል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy