Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በሶሪያ በተካሄደ አየር ድብደባ በትንሹ 58 ሰዎች በመርዝ ጋዝ ሳቢያ መገደላቸው ተነገረ

0 472

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኮየሶሪያ በአማጽ ይዞታ ስር ባለችው ካን ሼኩን ከተማ በመንግስት ወይም በሩሲያ የአየር ድብደባ መካሄዱን እና በጥቃቱ ዘጠኝ ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 58 ሰዎች በመርዝ ጋዝ መገደላቸውን የሶሪያ ተቃዋሚዎች ገለጹ፡፡

ማክሰኞ እለት በተካሄደው በዚሁ የአየር ጥቃት ተከትሎ አካባቢው ነዋሪዎች በጭሱ ምክንያት ታፍነው እራሳቸውን መሳታቸውን እና በአፋቸው በአረፋ ተደፍቆ መመልከቱን መቀመጫውን ብሪታኒያ ያደረገ የመብት ተሟጋች ድርጅት ተናግሯል፡፡

ደማስቆ እንደዚህ ያሉ መሳሪያዎችን እንደማትጠቀም የገለጸች ሲሆን ፤የሶሪያ ጦር ወዲያው በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን ማገኘት እንዳልተቻለ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

እንደ አልጀዚራ ጋዜጠኛው አለን ፊሸር ከቤሩት እንደዘገበው ፤በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም ሊልቅ ይችላል ብሏል፡፡

የሶሪያ ብሄራዊ አማጺያን ቡድን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፋጣኝ የመንግስታቱ ድርጅት ጸጥታ ምክርቤት ምርመራ እንዲያካሂድ ጠይቋል፡፡

እሁድ እለት በለቤትነታቸው የሩሲያ ሳይሆኑ እንዳለቀሩ የሚገመቱ የጦር ጄቶች በሰሜናዊ ኢድሊብ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ ባደረሱት ሶስት የአየር ጥቃቶች ቢያንስ አስር ሰዎች መቁሰላቸው እና የሆስፒታሉ ህንጻ መፍረሱ ተዘግቧል፡፡

ምንጭ ፦አልጀዚራ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy