Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በኦሮሚያ ክልል ወጣቶች የተዘዋዋሪ ፈንዱ ተጠቃሚ መሆን ጀምረዋል

0 385

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በኦሮሚያ ክልል ስራ አጥ ወጣቶች የወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድን በተመለከተ እስካሁን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲከናወኑ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዉ ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ ወጣቶች የፈንዱ ተጠቃሚ መሆን መሆን መጀመራቸዉን የክልሉ የኮሙኒኬሽን ቢሮ አመለከተ ፡፡

በቀጣይም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ስራ አጥ ወጣቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከቢሮዉ የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

በከተሞች በህገ ወጥ መንገድ የታየዙ ሼዶች፣ የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎች ላይ ማጣራት ማድረግ የተጀመረ ሲሆን እስካሁን በተደረገ ክትትል 824 ሼዶች በህገ ወጥ መንገድ መያዛቸዉ ስለተረጋገጠ ሼዶቹን ተመላሽ በማድረግ 429 በላይ ሼዶች በህዝብ ፊት ለስራ አጥ የገጠር እና የከተማ ወጣቶች በዕጣ እንዲተላለፉ ተደርገዋል፡፡ 395 ሼዶች ደግሞ ለወጣቶች በመተላለፍ ሂደት ላይ ናቸዉ፡፡

የማዕድን ቦታዎችን በተመለከተ እስካሁን በተደረገ እንቅስቃሴ ያለአግባብ የተያዙ 14,301.3 ሄክታር የማዕድን ማዉጫ ቦታዎችን  ከህገ ወጦች በማስመለስ ለወጣቶች የማስተላለፍ ስራ ተስርቷል፡፡ በማዕድን ዘርፍ እስካሁን በተደረገ እንቅስቃሴ  በ1978 ማህበራት ለተደራጁ 44, 869 ለሚሆኑ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡

ለወጣቶቹ ከሲሚንቶ ፋብሪካዎች  ጋር  አስተማማኝና ዘላቂ የገበያ ትስስር ለመፍጠር በክልሉ ከሚገኙ ትላልቅ የሲሚንቶ አምራች ኩባንያዎች ጋር ዉይይት ሲደረግ እንደነበርና በዚህም መሰረት ደርባ ሜድሮክ እና ዳንጎቴ ከተረደራጁ ወጣቶች የሲሚንቶ ግብዓት ማዕድናትን ለመግዛት ከወጣቶቹ ጋር ስምምነት መፈራረማቸዉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ኢስት ሴሜንት፣ ናሽናል ሴሜንት እና ሙገር በቅርቡ ከወጣቶቹ ጋር ዉል ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ የኦሮሚያ ክልል መንግስት የክልሉን ወጣቶች የስራ አጥነት ችግር ለመፍታት የሚያደርገዉን እንቅስቃሴ በመደገፍ የሲሚንቶ ምርቶችን ለወጣቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በመስጠትና በየዞናቸዉ በማከፋፈል ተጠቃሚ እንዲሆኑ  የጋራ ግንዛቤ ላይ መድረሳቸዉም ይታወሳል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy