Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በ7 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለሚገነባው የሲሚንቶ ፋብሪካ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

0 542

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አባይ ኢንዱስትሪ ልማት አክሲዮን ማህበር በ7 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጭ ለሚያስገነባው ሲሚንቶ ፋብሪካ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

በደጀን ከተማ አካባቢ ልዩ ስሙ ኮንቸር ሳሳበራይ እና ሜንጅየበዛ ቀበሌዎች የሚገነባው ፋብሪካ ሲጠናቀቅ፥ ለ1 ሺህ 690 ሰዎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ አድል ይፈጥራል ተብሏል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፥ የመሰረት ድንጋዩን ባስቀመጡበት ወቅት እንደገለጹት ፋብሪካው የኢንዱስትሪ ልማት ሽግግርን ከማፋጠን ባሻገር መዋቅራዊ ለውጥ ለማማምጣት የሚያስችል ነው።

አክሲዮን ማህበሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ራሱን በማደራጀት ለሚገነባው ስሚንቶ ፋብሪካ 250 ሄክታር መሬት ከሶስተኛ ወገን ነጻ በማድረግ በኩል ከአካባቢው መስተዳድሮች ጋር መስራቱን ተናግረዋል።

abay_cement.jpg

ለፋብሪካው ጥሬ እቃ ማምረቻ የሚውል 3 ሺህ 600 ሄክታር ቦታ በአባይ ሸለቆ የተፈቀደለት ሲሆን፥ ከአካባቢው ልማት ጋር ተጣጥሞ እንዲሄድ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም አስረድተዋል።

የፋብሪካው ግንባታም በአራት ዓመት ከአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ትናንት የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት ፋብሪካ፥ ግንባታው ሲጠናቀቅ በቀን 5 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንደሚያመርት የኢዜአ ዘገባ ያስረዳል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy