Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ባለሥልጣኑ የሌሊት ጉዞን ህጋዊ የሚያደርግ ፖሊሲ እያዘጋጀ ነው

0 431

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአገሪቱ ህገ ወጥ እንደሆነ  የተደነገገለትን  በሌሊት የሚሠጥ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን  ህጋዊ  የሚያደርግ ፖሊሲ እያዘጋጀ መሆኑን  የፌደራል የትራንስፖርት ባለሥልጣን አስታወቀ ።

እንደ ባለሥልጣኑ ገለጻ  በሌሊት ወቅት በህዝብ ትራንስፖርት አማካኝነት ለዓመታት ሲካሄዱ የቆዩት  ጉዞዎች ቀደም ብሎ በወጡት አዋጆች ህገ ወጥ መሆኑን ተደንግጓል ።

ባለሥልጣኑ  በህዝብ ትራንስፖርት አማካኝነት  በሌሊት የሚሠጥ ህገ ወጥ የትራንስፖርት አገልግሎትን  ለመከላከል እርምጃዎችን በመውሰድና የተለያዩ አሠራሮችን  ለመዘርጋት  ቢሞክርም  ችግሩን  ለማስወገድ አልቻለም ።

በአዲስ አበባ ከተማ  ዋልታ ቴሌቪዥን  ያነጋገራቸው የሌሊት ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች እንደሚናገሩት  በአገሪቱ  የመሠረተ ልማቶችና አሠራሮች በአግባቡ ከተዘረጉ  የሌሊት ጉዞን ህጋዊ ማድረግ ይቻላል ብለዋል ።

የፌደራል ትራንስፖርት  ባለሥልጣን ባለድርሻ አካላትን  በማሳተፍ የሌሊት ትራንስፖርት አገልግሎትን ህጋዊ የሚያደርግ  ፖሊሲን እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy