Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ብሔራዊ የጋራና የተቀናጀ የሳተላይት ቴሌቪዥን ስርጭት ማዕቀፍ ተዘጋጀ

0 972

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮ ሳት የተሰኘ ብሄራዊ የጋራ እና የተቀናጀ የሳተላይት ቴሌቪዥን ስርጭት ማዕቀፍ ተዘጋጀ።

የቴሌቪዥን ስርጭት ሳተላይት ማዕቀፉ የሚዲያ እኩልነትንና ፍትሃዊነትን እንዲሁም ተደራሽነትን በማረጋገጥ በመረጃ የበለጸገ ማህበረሰብ በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚናን ይጫወታል ተብሏል።

ኢትዮ ሳት የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሳተላይት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የተዘጋጀ ሲሆን፥ ለሳተላይት ኪራይ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ በማስቀረትና የመረጃውን ደህንነት በመቆጣጠር ረገድ ተስፋ የተጣለበት መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ተክለብርሀን ወልደአረጋይ ተናግረዋል።

ሳተላይቱ በሀገር ውስጥ ያለውን የሚዲያ ተደራሽነት በማስፋት ከሞገድ አጠቃቀም ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን በቀላሉ ለመቆጣጠር ያስችላልም ነው የተባለው።

በሀገር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ ሊደረግ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የሚገኘው ሳተላይቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ አስራ አንዱም ክልሎች የቴሌቪዥን ስርጭታቸውን በአንድ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው።

ከዚህ በተጨማሪም የሀገር ውስጥ የግልና የህዝብ የቴሌቪዥን ቻናሎችንም በሳተላይቱ በዝቅተኛ ክፍያ ለመጠቀም የሚያስችል አሰራርም ተዘርግቷል።

ሳተላይቱ ሌሎችም አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃኖችን መጠቀም እንዲያስችል ተደርጎ የተዘጋጀና ሲሆን፥ አሁን ላይ የቴሌቪዥን ስርጭት ፈቃድ አግኝተው የሚንቀሳቀሱ ተቋማት በቀላሉ ሳተላይቱን እንዲጠቀሙ ተደርጎም ነው የተዘጋጀው።

የፊታችን ሰኞ የሙከራ ስርጭቱን የሚጀምረው አዲሱ ሳተላይት አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናቆ በ2010 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ መደበኛ ተግባሩን ይጀምራል።

 

በሰለሞን ጥበበስላሴ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy