Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አልጀርስና ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ትብብራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ሊያሸጋግሩ ነው

0 933

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አልጀርስና ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ትብብራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ሲሰሩ መቆየታቸውን የአልጄርያ የውጭ ጉዳይና ዓለም ዓቀፍ ትብብር ሚኒስትር ራምታነ ላማራ ተናገሩ፡፡

4ኛው የአልጄሪያ እና ኢትዮጵያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአልጀርስ እየተካሄደ ነው፡፡

ዛሬ በሀገራቸው አስተናጋጅነት የሚካሄደው 4ኛው የአልጄሪያ እና ኢትዮጵያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ትብብሩን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ስምምነቶችን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

በስብሰባው ላይ ለመታደም አልጀርስ ከሚገኙት የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር በሀገራዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውንም ነው የውጭ ጉዳይና ዓለም ዓቀፍ ትብብር ሚኒስትሩ ላማራ የገለጹት፡፡

አልጄሪያና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገራት ግንባር ቀደሞቹ መሆናቸውን ያብራሩት ሚኒስትሩ፣ በአህጉሪቱ የጋራ ተግባራት ላይም የጎላ አስተዋጽኦ  እያበረከቱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢኮኖሚያዊ ትብብሩን  ወደ ላቀ ደረጃ የማሸጋገር ጥረቱ እኤአ በ2015 የሁለቱ ሀገራት ፕሬዝዳንቶች አልጀርስ ባካሄዱት ስብሰባ  ያስቀመጡትን አቅጣጫ መሰረት አድርጎ እየተከናወነ መሆኑንም ሚኒስትሩ ጨምረው  ገልጸዋል፡፡

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy