Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢህአዴግን ጨምሮ አገር አቀፍ ፓርቲዎች የሚያካሄዱትን ድርድር ያለገለልተኛ ወገን ለማካሄድ ከስምምነት ደረሱ

0 900

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢህአዴግን ጨምሮ አገር አቀፍ ፓርቲዎች የሚያካሄዱትን ድርድር ያለገለልተኛ ወገን  ለማካሄድ ከስምምነት ደረሱ።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያካሄዱት ድርድር ማን ይምራው በሚለው ሃሳብ ላይ ተወያይተው በጋራ ከስምምነት ለመድረስ ለስምንተኛ  ጊዜ ቀጠሮ ይዘው ነበር የተለያዩት ።

አብዛኞቹ ፓርቲዎች   ድርድሩ   ያለገለልተኛ  ወገን  ይካሄድ የሚለውን  አቋም  ሲያራምዱ፣    በሃሳብ  አንድ ነን  በሚል  ጥምረት   የፈጠሩ   ስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች  ማለትም መኢአድ፣ ሰማያዊ፣ ኢራፓ፣ ኢዴፓ፣መኢዴፓና ኢብአፓ ደግሞ   ድርድሩ    በገለልተኛ ወገን ይመራ  የሚለውን  አቋማቸውን  ወደ ፓርቲያቸው መልሰው ተወያይተው  ለመምጣት ለስምንተኛ ጊዜ ቀጠሮ  ይዘው ነበር።

በዚሁ መስረት ስድስቱም  ፓርቲዎች አንድ  ነን ባሉት  ሀሳባቸው ድርድሩ  ያለገለልተኛ   ወገን  ይመራ  የሚለውን  የጋራ ሀሳባቸውን አስቀምጠዋል።

ይህን ሰጥቶ የመቀበል አካሄዳቸውን  ኢህአዴግ  ለድሞክራሲያና   ለመድበለ  ፓርቲ እድገት  ወሳኝ  ነው ብሎታል።

ከዚህ በፊት በነበሩ መድረኮች ላይ  እንደተፀባረቅው ፓርቲዎቹ ከፈለጉ ውይይቱን  ያለኔ፣አልያም ቋሚ  ኮሚቴ በማደራጀት የማስቀጠል እድል በእጃቸው  መሆኑን ኢህአዴግ ተናግሯል።

በአሁኑ ሰዓትም በዚሁ ጉዳይ ላይ ፓርቲዎች አቋማቸውን  እየገለፁ ነው።

በዙር ይካሄድ  የሚሉ ፓርቲዎች በውይይቱ ላይ ሃሳባቸውን ያንፀባረቁ ሲሆን ከ21ዱ ተደራዳሪ  ፓርቲዎች  የሚወክሉን  የኮሚቴ አባላት ተመርጠው መድረኩ ይመራ የሚሉ ሀሰቦች ተንፀባርቀዋል።

ፓርቲዎቹ  የውይይት መድረኩን ማን ይምራው በሚለው ሀሳብ ላይ ከስምምነት ለመድረስ የሚያስችላቸውን ውይይት እንደቀጠሉ ነው።

ሪፖርተር ፥ ጥላሁን ካሳ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy