Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያና ካናዳ የንግድ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

0 1,023

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያና ካናዳ በመካከላቸው ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር ተስማሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በካናዳ ፓርላማ የውጭ ጉዳዮች ተጠሪ ሚስተር ኦማር አልግሃብራ የተመራ ልኡካን ቡድንን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ውይይቱን የተከታተሉት በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ፊሊፕ ቤከር እንደገለጹት፥ ሃገራቱ በንግድና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ተስማምተዋል።

አምባሳደሩ አያይዘውም ካናዳ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳዮች ተጠሪው መናገራቸውንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በካናዳ የልማት መርሃ ግብር ድጋፍ ከሚደረግላቸው ሃገሮች አንዷ መሆኗን ያስታወሱት አምባሳደሩ፥ የልዑካን ቡድኑ መሪ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸውን አብራርተዋል።

ሁለቱ ሃገራት ከልማት ትብብር በተጨማሪ የፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን በሚያጠናከሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያም ተወያይተዋል።

ሃገራቱ በፌዴራሊዝም ስርዓት የሚመሩ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ በዘርፉ ልምድ የሚለዋወጡበትን ሁኔታዎች ለማጠናከር መክረዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ካናዳ በየዓመቱ ለኢትዮጵያ ልማት የሚውል ከአንድ መቶ ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ ታደርጋለች።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy