Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በላሊበላ ተራራዎች ላይ ሳተላይትን በማምጠቅ ከአፍሪካ ከቀዳሚዎቹ ልትቀላቀል ነው

0 1,065

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 5 ዓመት ውስጥ ከአፍሪካ ሳተላይት ያመጠቁ አገራትን ልትቀላቀል ነው።

ከባህር ጠለል በላይ 2 ሺህ 500 ሜትር የሚሆነው ታሪካዊው የላሊበላ ሰንሰለታማ ተራራዎች በአለም ለሳተላይት ማጠቂያነት ተመራጭ ከሆኑት ቺሊና ሀዋይ ማዕከላት የማይተናነስ አቅም እንዳላቸው ዘ ኢኮኖሚስት የተሰኘው ድረ ገፅ በዘገባው ይዞ ወጥቷል።

በቀጣይም ዘርፉን ለማልማት ኢትዮጵያ የራሷን የጠፈር ሳተላይት ለማምጠቅ እየሰራች መሆኑን አምልክቷል፡፡

በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ውስጥም ኢትዮጵያዊ  ይዘት ያላት ሳተላይት በቻይና ተገንብታ ኢትዮጵያ ወደ ጠፈር ለማምጠቅ እየሰራች መሆኑን ድረ-ገፁ አስታውሷል፡፡

የሳተላይቱ ሞዴል የተቀረፀውም ሀገሪቱ በጠየቀችው መስፈርት እንደሆነና የሰብል ምርት፣ የአየር ሁኔታን እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን ለማሰባሰብ ጥቅም ላይ እንደሚውል ተመልክቷል፡፡

ሀገሪቱ የራሷ ሳተላይት ሲኖራትም በዘርፉ የውጭ ጥገኝነቷን እንድትቀንስ ያግዛልም ነው የተባለው፡፡

ኢትዮጵያ የራሷን ሳተላይቶች በጠፈር ምዕዋር ላይ ስታስቀምጥ በአፍሪካ ወደ ጠፈር ሳተላይት ካመጠቁ ጥቂት ሀገራት ተርታ እንደምትሰለፍ ተነግሯል፡፡

በአፍሪካ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካና ግብጽ በጠፈር ሳተላይት ያላቸው ሀገሮች ሲሆኑ ኬንያ፣ አንጎላና ጋና ደግሞ በዘርፉ ልማት ለመቀላቀል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ዘ ኢኮኖሚስት ጠቁሟል፡፡

የዘርፉ ልማት ለሀገሪቷ አያሌ ፋይዳ እንዳለው ይታመናል፡፡ ከዚህም ውስጥ የሀገሪቱን ማስተር ፕላን በመቅረጽ የመሬት ይገባኛል ግጭቶችን ለመፍታትና የግብርና ምርታማነትን ለማረጋገጥ ይጠቅማል ተብሏል፡፡

የከተሞችን እድገት ለማሻሻልና የኢንዱስትሪ ልማትን ለማፋጠን አገሪቱ ሳተላይት ማምጠቋ እንደሚጠቅማት ተመልክቷል።

ይሁንጂ ቴክኖሎጂው የሚጠይቀው የሀብት መጠን ከፍተኛ  በመሆኑ እንደኢትዮጵያ ላለ ታዳጊ  አገር ብዙ ወጪ ሊያስወጣት ይችላል ብሏል ዘግባው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy