Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በዓለም ፈጣን ኢኮኖሚ ካስመዘገቡ 5 ሃገራት መካከል አንዷ ሆነች

0 735

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ በዓለም ፈጣን ኢኮኖሚ ካስመዘገቡ አምስት ሃገራት መካከል በሁለተኛነት ተቀምጣለች፡፡

የዓለም ፋይናንስ ተቋም የዓለም ባንክ ሪፖርትን ጠቅሶ የ200 የዓለም ሃገራትን ኢኮኖሚያዊ እድገት በዝርዝር አስቀምጧል፡፡

ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ከድሃ ሃገራት ውስጥ ብትሆንም የሃገሪቱ በርካታ ሴክተሮች ኢኮኖሚውን ለማሳደግ በጥሩ ሂደት ላይ መሆናቸውን መረጃው አመልክቷል፡፡

በመረጃው መሰረትም ኢትዮጵያ በ8 ነጥብ 7 ኢኮኖሚያዊ እድገት ከዓለም አምስቱ ፈጣን የኢኮኖሚ ባለቤት ሃገራት መካከል በሁለተኛነት ተቀምጣለች፡፡

ቡታን በ11 ነጥብ 1 አንደኛ ፈጣን አድገት፣ኢትዮጵያ በ8 ነጥብ 7 ሁለተኛ ጋናና ኮቲዲቯር በእኩል 8 ነጥብ 1 ሶስተኛ ፣ህንድ በ7 ነጥብ 7 ኢኮኖሚያዊ እድገት አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጣቸውን መረጃው ይፋ አድርጓል፡፡

እንደአውሮፓ አቆጣጠር ከ1990ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በፍጥነት እያደገ መሆኑን መረጃው ጠቁሟል፡፡ እንደአውሮፓ አቆጣጠር ከ2004 እስከ 2014 ባሉት ዓመታትም በህዝብ መሰረተ ልማትና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ኢትዮጵያ ፈጣን እምርታዊ ለውጥ አስመዝግባለች፡፡

ሃገሪቱ አሁን በያዘችው ፍጥነት በማደግም እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2025 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ እንደምትሰለፍ መረጃው አረጋግጧል፡፡

ሃገሪቱ በሁሉም መስኮች በትክክለኛ መስመር ላይ በመሆኗና በተለይም የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሃገሪቱን ወደ ከፍተኛ እድገት ሊያስገቧት የሚችሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ላይ መሆኗን አብነት በማድረግ የያዘችው እቅድ እንደሚሳካ ዘገባው አስቀምጧል፡፡

ምንጭ፡-www.worldfinance.com

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy