Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ ከጀርመን ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር ታጠናክራለች-ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ

0 371

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ ከጀርመን ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ትብብር የበለጠ ለማሳደግ እንደምትሰራ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ገለፀዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀርመን ኢኮኖሚ ትብብር ልማት ሚንስትሩን ዶክተር ጋረድ ሙሉርን ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ባነጋገሩበት ወቅት፥ ኢትዮጵያ ከጀርመን ጋር በቴክኒክና ሙያ፣ በግብርና፣ በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም ሌሎች የትብብር መስኮች ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ከጀርመን ጋር ትሰራለች ብለዋል።

የጀርመኑ የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚንስትር ዶ/ር ጋርድ ሙለር በበኩላቸው ሀገራቸው በተለያዩ የልማትና የኢንቨስትመንት ዘርፎች ኢትዮጵያን መደገፍ እንደምትፈልግ ተናግረዋል።

የግብርናና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ እንቅስቃሴ ለመደገፍ የጀርመን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ-ነዋያቸውን በስራ ላይ እንዲያውሉ እናደርጋለን ነው ያሉት ሚኒስትሩ።

በኢትዮጵያ በአንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ በሰውና በእንስሳት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው ጀርመን የበኩሏን አስተዋፅኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣትና ማህበራዊ ፍትህን ለማስፈን እያደረገ ያለውን ጥረት የጀርመን ልኡክ አድንቋል።

የኢትዮጵያ እና የጀርመን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረውን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች የትብብር መስኮች ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ላይ ናቸው። ምንጭ፡-ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy