Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ዕፅ ይዞ መገኘት ለአንድ አመት ፅኑ እስራትና ለ300 ብር ቅጣት ዳረገ

0 563

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አብረሃም ሸዋ ይባላል፡፡ ግንቦት 25 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት በግምት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ ነው፡፡

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 መምህራን ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በሚጉዋዝበት ወቅት ባሳየው የተለየ ሁኔታ በአካባቢው ባሉ የፖሊስ አባላት አይን ውስጥ ይገባል፡፡

ወንጀልንና ወንጀል ነክ ጉዳዮችን የሚያነፈንፉት የፖሊስ አባላትም የአብረሀም ሁኔታ አንዳች የጥርጣሬ ስሜት ይፈጥርባቸውና አላመነቱም፣ ለደቂቃዎች በማስቆም ይፈትሹታል፡፡

ጥርጣሬው እውን ሆኖ በግለሰቡ ኪስ ጠቅላላ ክብደቱ 277 ግራም የሆነ የካናቢስ  ዕፅ ያገኛሉ፡፡

ፖሊስ ይህን አደንዛዥ ዕፅ ለማጣራትም ወደ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ በመላክ የፎረንሲክ ምርመራ እንዲደረግ ያደርጋል፡፡

የምርመራው ውጤቱም የካናቢስ ዕፅ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ሂደቱን ያጠናቅርና ለፌደራሉ ዓቃቤ ህግ እነሆ ይለዋል፡፡

የፌደራሉ ዓቃቤ ህግም የምርመራ መዝገቡን ከበቂ ማስረጃ ጋር ለፌደራሉ  ከፍተኛው ፍርድ ቤት ስምንተኛ ወንጀል ችሎት በማቅረብ የክርክር ሂደቱን ይቀጥላል፡፡

ስምንተኛው ወንጀል ችሎትም የግራ ቀኙን ያዳምጥና በሚያዝያ 13 ቀን 2009 የቅጣት ውሳኔውን ይሰጣል፡፡

በቅጣት ውሳኔው ላይ አቃቤ ህግ ድርጊቱ ምን ያህል የከፋ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል በማብራራት ቅጣቱ  እንዲከብድ ያቀርባል፡፡

ተከሳሹም የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑን ገና  ወጣትና መልካም ስነምግባር ያለውና ከዚህ ቀደም ምንም አይነት የወንጀል ድርጊት ያልፈፀመ እንደሆነ በማስረዳት ቅጣቱ እንዲቀልለት ይጠይቃል፡፡

በመጨረሻም ችሎቱ የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 1/ሀ/525 በመጥቀስ በሀገሪቱ ህግ እንዳይመረት፣ እንዳይዘዋወርና እንዳይጠቀም የተከለከለ መሆኑን በማብራራት በአንድ አመት ፅኑ እስራትና በ300 ብር እንዲቀጣ በመወሰን ፋይሉን ዘግቷል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy