Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢህአዴግ ምክር ቤት የሁለተኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን የሁለተኛው ዓመት አጋማሽ አፈፃፀምን ሊገመግም ነው

0 342

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የሁለተኛው ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን የሁለተኛ ዓመት አጋማሽ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ነገ እንደሚጀምር የግንባሩ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ኢህአዴግ በይፋ የጀመረውን በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ በአመራሩ፣ በአባል፣ በሠራተኛውና በመላው ህዝብ እንዲታይ የተቀመጠው አቅጣጫ የደረሰበትን ደረጃ እንደሚገመግም ይጠበቃል፡፡

የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር ወኪል የሆኑት ትምክህትና ጠባብነት፣ ስልጣንን ለግል ጥቅም የማዋል አመለካከትና ተግባራት ድርጅቱንና አገራዊ የህዳሴ ጉዞውን የሚፈታተኑ አደጋዎች መሆናቸውን ጽሕፈት ቤቱ በመግለጫው አመልክቷል።

በተለይም ህዝብን ጨምሮ በየደረጃው ትግል እንዲደረግባቸው የተቀመጡ የጥልቅ ተሃድሶ አቅጣጫዎች ምን ላይ እንደደረሱ ምክር ቤቱ በዝርዝር እንደሚገመግም ተመልክቷል።

ምክር ቤቱ ነገ በሚጀምረው መደበኛ ስብሰባው በየደረጃው ህዝቡ ሲያነሳቸው የነበሩ እና “ፈጣን ምላሽ ያስፈልጋቸዋል” ተብለው የተለዩ ጉዳዮችን አፈፃፀም ይመለከታል፡፡

የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት በተመለከተም የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ እንቅስቃሴው የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ነው መግለጫው ያመለከተው።

የኢህአዴግ ምክር ቤት በግምገማው የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን የሁለተኛው ዓመት አጋማሽ አፈፃፀም  የማክሮ ኢኮኖሚ፣ በኢኮኖሚና ማሕበራዊ ዘርፍ የተቀመጡ እቅዶች አፈጻጸም ይፈትሻል።

በተጨማሪም በመድረኩ የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት፣ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አፈፃፀሞችን  በመፈተሽ ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡

በአገራችን ደቡብና ደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች በተፈጠረው ድርቅ ምክንያት የሰው ህይወት ሳይጠፋና በእንስሳት ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በራስ ዓቅም ለመቋቋም እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችንም ምክር ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚመለከት ጽሕፈት ቤቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ ጠቁሟል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy