Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፓክስ ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፈ

0 465

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ የምግብ አገልግሎት የአፍሪካ ምርጥ በመሆን የ2017 የፓክስ ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፈ።

አየር መንገዱ በጀርመኗ ሀምቡርግ ከተማ መጋቢት 27 ቀን 2009 ዓ.ም በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት ያሸነፈው በበረራ ወቅት ለመንገደኞች በሚሰጠው አገልግሎት በፓክስ መጽሄት አንባቢያን ቀዳሚ ሆኖ በመመረጡ ነው።

በበረራ አገልግሎት ዙሪያ ያተኮረው ፓክስ መጽሄት ባካሄደው የኦንላይን ድምጽ ማሰባሰብ 25 ሽልማቶች ለአገልግሎት ሰጪዎች ተሰጥተዋል።

ከእነዚህ መካከል የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራ የምግብ አገልግሎት የአፍሪካ ምርጥ በመሆን የዓመቱ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል።

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የመጽሄቱ አንባቢያን ከፍ ባለና በማያሻማ ድምጽ የኢትዮጵያን አየር መንገድ የአፍሪካ ምርጡ የበረራ ምግብ አገልግሎት ሰጪ ብለው በመምረጣቸው ምስጋና አቅርበዋል።

አየር መንገዱ “በሁለንተናዊ አገልግሎቱ ደንበኞች ተኮር እንዲሆን በትጋት መስራቱን ይቀጥላል” ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደንበኞቹ የሚያቀርባቸው የቻይና፣ የጣልያን፣ የህንድና ሌሎች አገራት ምግቦችና ፍራፍሬዎች ትኩስና ተፈጥሯዊ እንደሆኑም ተናግረዋል።

አየር መንገዱ በቅርቡ በቀን 100 ሺህ የታሸጉ ምግቦችን በማምረት ማቅረብ የሚችል የበረራ ምግብ ማዘጋጃ ማዕከል መገንባቱ የሚታወስ ነው።

በበረራ ዘርፍ የ2025 ራዕዩ የ15 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በመንደፍ በአፍሪካ መሪ የዘርፉ ማዕከል ለመሆን እየሰራ መሆኑን አየር መንገዱ ገልጿል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy