Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኦሮሚያና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች በ1997 የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ለመተግበር ተስማሙ

0 665

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኦሮሚያ እና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች በ1997 የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ለመተግበር ተስማሙ።

የሁለቱ ክልሎቹ ርዕሰ መስተዳደሮች በፈረሙት ስምምነት ህዝበ ውሳኔውን መሰረተ በማድረግ የአስተዳደር ወሰን ያልተካለለባቸው አካባቢዎችን ለማካለል ተስማምተዋል።

በተጨማሪም ሁለቱ ክልሎች ዛሬ በተፈራረሙት ሰነድ የ1997 ዓ.ም ህዝበ ውሳኔን ተከትሎ የተደረሰውን የአስተዳደራዊ የወሰን ስምምነት ተቀብለው ተግባራዊ ለማድረግ ከስምምነት ደርሰዋል።

ሁለቱም ክልሎች የስምምነቱን ሰነድ በተፈራረሙ በሶስት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አስተዳደራዊ ወሰኑን ለህዝብ ይፋ በማድረግ ማጠቃለል ላይም ተስማምተዋል።

እንዲሁም አጎራባች ዞኖች ወረዳዎች እና ቀበሌዎችን በልማት እና መልካም አስተዳደር ማስተሳሰር የሚለውም የስምምነቱ ሰነድ አካል ነው።

በሁለቱ ክልል መንግስታት በኩል የውሳኔውን አፈፃፀም የሚያስተጓጉሉ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በጋራ መስራት፤ ከስምምነቱ በኋላ አጎራባች አካባቢዎች ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ ኬላዎችን ማስወገድ የሚሉትም በስምምነቱ ላይ ተካተዋል።

በህዝበ ውሳኔው እና አስተዳደራዊ ወሰን የማካለል ስምምነት መሰረት በሁለቱ ክልሎች የሚኖሩ ማህበረሰቦች ህገ መንግስታዊ መብታቸውን መጠበቅ የሚለ የስምምነቱ አካል ነው።

አስተዳደራዊ ወሰን ከማካለል ስምምነት በኋላ በማናቸውም መልኩ ማህበረሰቦችን አለማፈናቀል፤ በመኖሪያ አካባቢያቸው ይኖራሉ የሚለው እና ከአስተዳደራዊ ወሰን ማካለል ጋር ተያይዞ የታሰሩ ሰዎች ካሉ እንዲለቀቁም ማድረግም በስምምነቱ ውስጥ ተካቷል።

የፌደራል እና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚንስትሩ አቶ ካሳ ተክለብርሀን ሰነዱ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠሩ ግጭቶች ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች የቃል ኪዳን ሰነድ ነው ብለዋል።

የሁለቱ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች በበኩላቸው፥ ስምምነቱን በተቀመጠለት ጊዜ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy