Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የካይሮ ፍርድ ቤት ሁለቱ የቀይ ባህር ደሴቶች ለሳዑዲ እንዲሰጡ ወሰነ

0 553

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በካይሮ አስቸኳይ ጉዳዮችን የሚመለከተው ፍርድ ቤት የቀይ ባህር ደሴቶች ለሳዑዲ ዓረቢያ ተላልፈው እንዲሰጡ ወሰነ።

የካይሮው ፍርድ ቤት የሀገሪቱ ከፍተኛ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት በቀይ ባህር ደሴቶቹ ጉዳይ ምንም አይነት የመወሰን ስልጣን የለውም ብሏል።

አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ጥር ወር ላይ ቲራን እና ሳናፊር የተሰኙ በቀይ ባህር የሚገኙ ደሴቶች የግብፅ ናቸው የሚል ውሳኔ አሳልፎ ነበር።

ባለፈው የፈረንጆቹ አመት ሚያዚያ ወር የግብጽ መንግስት ሁለቱ ደሴቶች ለሳዑዲ ዓረቢያ ተላልፈው ይሰጡ ማለቱን ተከትሎ ከበርካታ ግብፃውያን ተቃውሞ ገጥሞታል።

በዚህም ምክንያት የሀገሪቱ ከፍተኛ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የግብፅ መንግስት ያሳለፈውን ውሳኔ ውድቅ በማድረግ ደሴቶቹ የግብፅ ሉዓላዊ ግዛት ናቸው የሚል ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

ይህን የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመሻር ነው ታዲያ የካይሮ ፍርድ ቤት የግብፅ መንግስትን አቋም ደግፎ ደሴቶቹ የካይሮ ሳይሆን የሪያድ ግዛቶች ናቸው ያለው።

በደሴቶቹ ባለቤትነት ላይ የግብፅ ከፍተኛ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት እና የካይሮ ፍርድ ቤት ያሳለፉት ሁለት የተለያየ ውሳኔ እልባት የሚያገኘው የግብፅ ከፍተኛ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት በሚያሳልፈው የመጨረሻ ውሳኔ ይሆናል ተብሏል።

ግብፅ እነዚህን ሁለት ደሴቶች እንደ አውሮፓውያኑ ከ1950ዎቹ ወዲህ በብቸኝነት እያስተዳደረቻቸው ትገኛለች።

ምንጭ፦ ሲጂቲኤን አፍሪካ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy