Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሀሰተኛ ሰነድ ሲጠቀሙና ፈቃድ ሳያሳድሱ ሲንቀሳቀሱ አግኝቷቸው ባገዳቸው ተቋራጮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

0 669

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የቁጥጥር ቡድን ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም እና የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳያሳድሱ ሲንቀሳቀሱ አግኝቷቸው ከስራ አግዷቸው በነበሩ 177 የግንባታ ተቋራጮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ።

ሚኒስቴሩ ያሳለፈው ውሳኔ የተመለከተው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ እና የፌደራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ባደረጉት ክትትል ፈቃድ ሳያድሱ እና የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው በተጭበረበሩ ሰነዶች በህገወጥ መንገድ በስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ እና ከደረጃ 4 እስከ 10 ያሉ ተቋራጮች ናቸው።

በዚህም መሰረት 141 ተቋራጮች መንግስት እና ህዝብን ለመጨረሻ ጊዜ ይቅርታ የጠየቁ ተገቢ ስልጠና ተሰጥቷቸው እና ወቅታዊ ብቃታቸው ተረጋግጦ ፈቃዳቸውን አሳድሰው በአዲስ መልክ ወደ ስራ እንዲገቡ ይቅርታ ተደርጎላቸዋል ብሏል።

እነዚህ ተቋራጮች ከመነሻቸው ህጋዊ ፈቃድ የነበራቸው ነገር ግን በሂደት ደረጃቸውን በሀሰተኛ ሰነድ ያሳደጉ፣ ፈቃድ ያላደሱ እና ሀሰተኛ የባንክ የብድር ሰነዶችን ያቀረቡ መሆናቸውን ነው ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ያመለከተው።

በህግ ተጠያቂ ያልተደረጉት ለምንድን ነው ተብሎ የተጠየቀው ሚኒስቴሩ፥ “እነዚህ ተቋራጮች በርካታ ዜጎችን ቀጥረው እያሰሩ ያሉ በመሆናቸው ቢዘጉ ጉዳቱ በሰፊ ሰራተኛ ላይ ይከፋል በሚል እና ተቋራጮቹም ህዝብን ይቅርታ በመጠየቃቸው በይቅርታ ወደ ስራ እንዲመለሱ ተወስኗል” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

ሌሎች ህገወጥ ሰነዶችን ተጠቅመው ዓየር በዓየር ሲሰሩ የነበሩ ያላቸው 36 ተቋራጮችን ግን ይቅርታው እንደማይመለከት ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በግንባታው ዘርፍ ሀሰተኛ የስራ ተቋራጭ የብቃት ማረጋገጫ ሰነድን ለመከላከል የሚያስችለውን ስርአት እየዘረጋ መሆኑን ሚኒስቴሩ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ መግለፁ ይታወሳል።

በግንባታው ዘርፍ በተለይም በቤት እና በመንገድ ግንባታዎች በተቀመጠው ጊዜ አለመጠናቀቅና ጥራትን ጠብቆ አለመገንባት በዘርፉ ከሚቀርቡ ቅሬታዎች መካከል ተጠቃሾች ናቸው።

የተቋራጮቹ አቅም ማነስ ደግሞ በበርካቶች ዘንድ በዋነኛ የችግር ምንጭነት የሚጠቀስ ጉዳይ ነው።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት የስራ ተቋራጮች ሀሰተኛ የኮንስትራክሽን እቃዎች ማረጋገጫን በማዘጋጀትና በመከራየት ፈቃድ ማውጣታቸው እንዲሁም፥ በተመሳሳይ እቃዎች የተለያዩ ክልሎች ላይ የደረጃ ፈቃዱን ማውጣት መቻላቸው ለሚከሰተው የአቅም ማነስ ችግር መንስኤም ነው።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy