Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የጉዞ ፍቃድ የወሰዱ 2 መቶ ኢትዮጵያዊያን አዲስ አበባ ገብተዋል፡- ውጭ ጉዳይ

0 451

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ያወጣውን አዋጅ ተከትሎ እስከ አሁን ድረስ በህገ ወጥ መልኩ የሚኖሩና የጉዞ ሰነድ ያወጡ 2 መቶ ኢትዮጵዊያን ወደ አገር ቤት መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አስታውቋል፡፡

አዋጁን ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት የሚመለሱ ዜጎች የግል መገልገያ ዕቃዎቻቸውን ከማንኛውም ቀረጥና ታክስ ነፃ በሆነ መንገድ ወደ አገር ቤት እንዲያስገቡ መፍቀዱንም የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል፡፡

ዜጎች ይኖሩበት ከነበረው ሳዑዲ ዓረቢያ  ሲወጡ ይዘዋቸው የሚመጡት የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ የጋዝ ምድጃ፣ ቴሌቪዥን፣ ኮምፒውተር 21 ዓይነት የግል መገልገያ ዕቃዎችን ይዘው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተፈቅዶላቸዋል፡፡

ሳውዲ አረቢያ ያለመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ የሚኖሩ የውጭ ሀገራት ዜጎች በ90 ቀናት ያለቅጣት አገሪቱን ለቀውእንዲወጡ  ያወጣቸውን  አዋጅ ተከትሎ የሁሉም አገራት ዜጎች ናቸው ወደየአገሮቻቸው አየተመለሱ ያሉት፡፡

የሳውዲ መንግስት ህገወጥ የሚላቸው በህገወጥ መንገድ የሳውዲን ደንበሮች አቋርጠው የገቡ ስደተኞች፣ ቋሚ ቦታ ሳይኖራቸው በመዘዋወር በህገወጥ መንገድ የሚሰሩ ስደተኞች፣ የስራ እና የመኖሪያ ፈቃድ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ የውጭ አገር ነዋሪዎች፣ የስራ ፈቃድ ኖሮት ነገር ግን የመኖሪያ ፈቃድ መታወቂያ ካርድ የሌላቸው የውጭ አገር ዜጎች ነዋሪዎች፣ ለኡምራና ሃጂ ሂደው በዚያው የቀሩ/ የቆይታ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ነዋሪዎች፣ እና ያለ ሀጂ ፈቃድ የተጓዙ አማኞች ዋነኛዎቹ ናቸው፡፡

በአዋጁ የተሰጠውን የጊዜ ገደብ አክብረው ለሚወጡ የውጭ አገር ዜጎች መከናወን የሚገባቸው ጉዳዮች፥

  • በሳውዲ አረቢያ ያለመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ የሚኖሩ የውጭ ሀገራት ዜጎች ከመጋቢት 21 እስከ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም በ90 ቀናት ውስጥ፣ በሚኖሩበት አካባቢ በሚገኙ የኢሚግሬሽን ጽ/ቤቶች የመውጫ ቪዛ ወዲያውኑ እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡
  • ያለምንም ቅጣት በራሳቸው ትራንስፖርት ወጪ በፈቃደኝነት ከሀገሪቱ እንዲወጡ ይደረጋል፣ በተሰጠው የ90 ቀን የጊዜ ገደብ ውስጥ አገሪቱን ለቆ ለሚወጣ የውጭ አገር ዜጎች የጉዞ ሰነዶችን ከሚመለከተታቸው አካላት መውሰድ ይችላል፡፡
  • በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚወጡት በህጋዊ መንገድ ወደ ሳውዲ አረቢያ መመለስ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ከአገሪቱ በሚወጡበት ጊዜ የጣት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም፡፡

ከምህረት ጊዜው መጠናቀቅ በኋላ ለህገ ወጦቹ ከለላ የሰጠ ወይም የቀጠረ ማንኛውም ግለሰብ ሆነ የንግድ ተቋም በሀገሪቱ በወጡት የወንጀል ህጎች እንደሚጠየቅና የእስራትና ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እንደሚያስከትልበአዋጁ  ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚስቴር

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy