Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

“ደረጃው ይለያያል እንጂ ብኣዴን እና ህወሓት፣ በኦህዴድ እና በህወሓት፣ በብኣዴን እና ደኢህዴን ጓዶች መካከል መጠራጠር ነበር።

0 1,108

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

“ደረጃው ይለያያል እንጂ ብኣዴን እና ህወሓት፣ በኦህዴድ እና በህወሓት፣ በብኣዴን እና ደኢህዴን ጓዶች መካከል መጠራጠር ነበር።
ይህ ጥርጣሬ የፈጠረው የሻከረ የእርስ በርስ ግንኙነት በግልፅ ውይይት ፣በመገማገም እና በመተማመን ችግሩ ተፈትቷል ።”
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር #አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ
ጠቅላይ ሚንስትሩ በዛሬው እለት በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ዙርያ ከጋዜጠኞች ጋር ተወያይተዋል።
አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በውይይታቸው ኢህኣዴግ እስከ ህዝብ ድረስ ወርዶ ባደረገው ጥልቅ ተሀድሶ የነበሩ ስጋቶች መቀልበሳቸውን አውስተዋል ። ይህ ም የተረጋገጠውም ከህዝቡ እና በህዝቡ ውስጥ ባለው ሁኔታ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በትናንትናው እለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው ሪፖርት በጥልቀት የተጠና እና በምርመራ የተገኘ ውጤት መሆኑን እና ከጥልቅ ተሀድሶው ቡኃላ ኮሚሽን መስርያ ቤቱ ለውጥ ማምጣቱን
እና አቅሙ እየጎለበት መምጣቱን የሚያሳይ እንደሆነ ገልፀው
በሪፖርቱ መሰረት መንግስት እርምጃ እንደሚወስድ እና ከችግሩ ጋር በተያያዘ ተለይተው በህግ መጠየቅ እንደተጀመረም ተናግረዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ኣንዳንድ ኣካላት በኮሚሽኑ የውጭ አካላት ገብተው የማጣራት ስራውን ለምን ኣይሰሩም የሚል ጥያቄ እንደሚያነሱ ግን ደግሞ
የውጭ ኣካላት በኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ጉዳይ ዙርያ እንዲመረምሩ ኢትዮጵያ እንደማትፈቅድ እና ኮሚሽን መስራቤቱ ኣቅም በመፍጠር የሌላ ኣካል እጅ ሳይኖርበት ያገኘውን መረጃ ለህዝብ ይፋ
በማድረግ የራሳችንን ችግር ራሳችን በመፍታት የሰብኣዊ መብት በሀገራችን እንዲከበር መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy