Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ዶክተር መረራ ጉዲና በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ላይ 11 ገጽ ያለው የክስ መቃወሚያ አቀረብ።

0 423

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ዶክተር መረራ ጉዲና በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ላይ 11 ገጽ ያለው የክስ መቃወሚያ አቀረብ።

የክስ መቃወሚያው የቀረበው በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ነው።

ዛሬ በቀረበው የክስ መቃወሚያ በዋናነት ዶክተር መረራ“ ክሴ ከእነ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ እና ጃዋር መሀመድ ጋር አብሮ ሊታይ አይገባም፤ የእኔ የህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ሊቀ መንበርነት ከእነሱ አላማና አፈጻጸም ጋር የማይገናኝ በመሆኑ ሊነጠል ይገባል“ ይላል።

“ቤልጂየም ብራስልስ ለህዝባዊ ስራ ነው የሄድኩት፤ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቁጥር 11/2009 ዓ.ም መሰረት ኮማንድ ፖስቱ ያወጣው የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መመሪያ አንቀጽ 2/1 ስር የተመለከተውን ተላልፏል የተባለውን እቃወማለሁ“ ሲሉ በመቃወሚያቸው ጠቅሰዋል።

“በ2008 እና 2009 ዓ.ም በአማራና በኦሮሚያ ክልል ለተከሰተው ሁከት እና አለመረጋጋት እኔ ልጠየቅ አይገባም“ ሲሉም ተቃውሞዋቸውን አቅርበዋል።

“የኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ ተብሎ በሚጠራው ሚዲያ ላይ ስለ ኢሬቻም ሆነ የሁከት ጥሪ በሚመለከት ቃለ ምልልስ አላደረኩም“ ሲሉም የቀረበባቸውን ክስ ተቋውመዋል።

በአጠቃላይ በክሱ የወንጀል ስነስርአት ህግ ቁጥረ 111፣ 112 እና 130 አንቀጾች ዝርዝር ነገሮች ይቀሩታል በማለት በ11 ገጽ አያይዘው አቅርበዋል።

መቃወሚያውን የሰማው ፍርድ ቤትም መቃወሚያው ላይ የአቃቤ ህግ አስተያየትን ለመስማት ለሚያዚያ 26 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy