Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ዶክተር ወርቅነህ አልጀርስ ናቸው

0 520

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በ4ኛው የኢትዮ አልጀሪያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ለመካፈል አልጀርስ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ አልጀርስ ሲገቡ በአልጀሪያ አቻቸው ራምቴን ላማምራ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

4ኛው የኢትዮ አልጀርስ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ የሁለቱን ሀገራት የጠበቀ ግንኙነት የበለጠ ያጎለብታል ተብሎ ይጠበቃል።

ሀገራቱ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዘርፎች ለማስፋትም ይመክሩበታል።

በስብሰባው ማጠናቀቂያ ላይ የተለያዩ ስምምነቶች እና የመግባቢያ ሰነዶችም እንደሚፈረሙ ነው የሚጠበቀው።

workneh.jpg

ከሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባው ጎን ለጎንም የኢትዮጵያ እና አልጀሪያ ባለሙያዎች የሁለቱ ሀገራት የትብብር ማዕቀፎችን የሚገመግሙ ሲሆን፥ የትብብር መስኮቹን ለማስፋት በሚያስችሉ ጉዳዮችም ላይ ይመክራሉ።

ኢትዮጵያ እና አልጀሪያ ለረጅም አመታት የዘለቀ ግንኙነት አላቸው።

ሁለቱ ሀገራት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1960ዎቹ መግቢያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን መጀመራቸው ይታወሳል።

አልጀሪያ በ1976 በአዲስ አበባ ኤምባሲዋን የከፈተች ሲሆን፥ ኢትዮጵያም በ2016 ኤምባሲዋን በአልጀርስ መክፈቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውሷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy