Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ፕሬዚዳንት ኤል ሲሲ ግብጽ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በፍጹም ጣልቃ እንደማትገባ ገለጹ

0 414

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የግብጹ ፕሬዚዳንት ኤል ሲሲ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንደማትገባ እና ሀገሪቱን ሊጎዱ ከሚችሉ ኃይሎች ጋር በፍጹም እንደማትተባበር ገለጹ ፡፡

የኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ዛሬ ከግብጹ ፕሬዚዳንት ኤል ሲሲ ጋር የተገናኙ ሲሆን፥በጋራ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

እንደ ግብጹ አልሃራም ኦንላይን ዘገባ ፥ ፕሬዚዳነት ኤል ሲሲ በመግለጫቸው ግብጽ በማንኛውም መንገድ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እንደማትገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡በዚሁ ወቅት የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ኢትዮጵያ የግብጽ ህዝብ ጥቅሞች በፍጹም የመጉዳት አንዳችም ፍላጎት እንደሌላት አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ እና የግብጽ ህዝቦች በታሪካ እና በአባይ ወንዝ የቆየ ትስስር እንዳላቸው ያስታወሱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፥ ሀገሪቱ በተፈጥሮ ሀብቷ የመጠቀም መብቷን በማክበር የሁለቱን ሀገራት ጥቅሞቻቸውን በጋራ ለማረጋገጥ  አብረው ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ከፕሬዚዳንቱ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር በሁለትዮሽ ትብብሮች ዙሪያ ተነጋግረናል ነው ያሉት፡፡

የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ በበኩላቸው፥ ከኢትዮጵያው አቻቸው ጋር “በግልጽነት እና በቅንነት“ መወያየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት ባለስልጣናት በየሁለት ወሩ እየተገናኙ እንደሚወያዩ እና የሀገራቱን ግንኙነቶች እንደሚያሻሽሉ የገለጹት ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ፥ ካይሮ በቅርቡ ፕሬዚዳንት ኤል ሲሲ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ያሉበት ከፍተኛ የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ እንደምታዘጋጅ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡
ምንጭ፦አልሃራም ኦንላይን

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy