Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ህንድ ለአለም ጤና ድርጅት መሪነት ለሚወዳደሩት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ድምጿን ልትሰጥ እንደምትችል ተገለፀ

0 1,335

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ህንድ ለአለም ጤና ድርጅት መሪነት ለሚወዳደሩት  ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ድምጿን  ልትሰጥ እንደምትችል  ተገለፀ፡፡

ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኝነት መልካም መሆኑና በዲፖሎማሲያዊ ጥረት ህንድ ከቀረቡት ሶስት ዕጩዎች ዶክተር ቴድሮስን ምርጫዋ የማድረጓ እድል የሰፋ ማሆኑን ከአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር  ያገኘውን መረጃ በመጥቀስ ዘሂንዱ ዘግቧል፡፡

እንደዘገባው ከሆነ ህንድ ለድርጅቱ ዕጩ ተፎካካሪ ከሆኑት  ከእንግሊዛዊ  ዴቪድ ናባሮና ከጎረቤቷ ፓኪስታናዊ  ሳኒያ ኒሽታር  ጋር በማወዳደር ነው ድጋፏን ለዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ልትሰጥ እንደምትችል የተገለፀው፡፡

በተለይም ህንድ ከፓኪስታን ጋር ባላት ያልሰመረ ግንኙነት ምክንያት ኢሲያን ወክለው ለቀረቡት እጩ ድጋፍ የመስጠት እድሏ አናሳ መሆኑን ዘገባ አመልክቷል፡፡

የዘንድሮው ለአለም  ጤና ድርጅት  ዋና ዳይሬክተርነት የሚደረገው የመጨረሻው ፍኩክር በ194 አባል አገራት በቀጥታ ተሳትፎ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሳተፉበት መድረክ   ነው የሚለየው፡፡

ከሶስቱ የመጨረሻ ዕጩዎች ከግንቦት 14-23 ፣2009 በሚደረገው የአለም  ጤና ድርጅት ጉባኤ መዝጊያው ላይ  የሚለይ ሲሆን አሸናፊው ዕጩ ሰኔ 24፣ 2009 ስራውን በይፋ ይጀምራል፡፡

ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ድርጅቱን ለመምራት ከቀረቡት አምስት እጩዎች አብላጫ ድምፅ በማግኘት ነበር ባለፈው ጥር ከሶስቱ ጎራ የተቀላቀሉት፡፡

በአፍሪካ 54ቱም አገራት ሙሉ ድጋፍ ያላቸው ዶክተር ቴድሮስ የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነትን  ቁልፍ ቦታ ያገኛሉ የሚለው ግምት ወደሳቸው የደፋ ይመስላል፡፡

አዲሱ ተመራጭ የድርጅቱን የፋይናስ ክፍተት በመሙላትና ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት በሚጠይቀው ቦታ ላይ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት በተለይም በአፍሪካ የተከሰተውና ለ11 ሺህ ሰዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት የሆነው የኢቦላ ወረርሽን የሰጠው ምላሽ አናሳ በመሆኑ በተደጋጋሚ መወቀሱ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፤ ዘ ሂንዱ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy