Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

መቀመጫቸውን በግብፅ አድርገው በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውን ሁከት ሲመሩ በነበሩ ተቋማት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው- ጠ/ሚ ኃይለማርያም

0 352

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

መቀመጫቸውን በግብጽ ካይሮ አድርገው በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውን ሁከት ሲመሩ በነበሩ ተቋማት ላይ የሀገሪቱ መንግስት አርምጃ መውሰድ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒሰተር ሀይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ።

ሁለቱ ሀገራት በጋራ ባደረጉት ውይይት ነው ግብጽ በኢትዮጵያ አፍራሽ ሚናን የሚጫወቱ ተቋማትን ላለማስተናገድ ቃል የገባቸው።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ቆይታ አድርገዋል።

በቆይታቸውም ከሀገሪቱ ወቅታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮሚያዊ ጉዳዮች አንስቶ አስከ ቀጠናዊ አጀንዳዎች ድረስ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢ ተከስቶ ከነበረውን ሁከት አስመልክቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበውሪፖርት ዙሪያ ከጋዜጠኞች ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

በሪፖርቱ ላይ እንደተቀመጠው በሁከቱ ውስጥ ሚና ነበራቸው ተብለው የተለዩ አመራሮችን ጨምሮ የተለያዩ አካላትን በትክክል ተጠያቂ ለማድረግ መንግስት ቁርጠኛ ነው ወይ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝም፥ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያቀረበው ሪፖርት ለየት የሚያደርገው በትክክል መጠየቅ ያለባቸውን ሰዎች በግልፅ ማስቀመጡ ነው፤ ይህም የኮሚሽኑ አቅም እየጠነከረ መምጣቱን ያመለክታል ብለዋል።

ግለሰቦቹን ተጠያቂ ከማድረግ አንጻርም መንግስት ምንም አይነት ችግር የለበትም፤ ሪፖርቱ ባስቀመጠው መልኩ አስፈላጊው ነገር ያደርጋል ሲሉም ተናግረዋል።

ከኮሚሽኑ ገለልተኝነት ጋር ተያይዞ ለተነሳላቸው ጥያቄም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ፥ “እኛ በዋናነት መታመን የምንፈልገው በህዝባችን ነው፤ በሁከቱ የደረሰው ጉዳት በአጠቃላይ በህዝቡ የሚታወቅ ነው ስለዚህ የሚደበቅም የሚሸፈንም ነገር የለንም” ብለዋል።

ሌሎች ተቋማት ጉዳዩን ለማጥናት ጥያቄ አቅርበው ነበር፤ ነገር ግን ይህ ጉዳይ እኛን የሚመለከት በመሆኑ እና የሉአላዊነት ጉዳይ በመሆኑ አልፈቀድንላቸውም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አጥንቶ ያቀረበው ሪፖርት በጄኔቫ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተቀብሎት እውቅና መስጠቱን እና ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመስራት ላይ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ እና የግብፅ ግንኙነትን አስመልክቶም ኢትዮጵያ በውጭ ሀገራት ላይ ያላት ፖሊሲ በመተማመን፣ በመከባበር፣ በጋራ ተጠቃሚነት እና በሰላም አብሮ መኖር ላይ ያተኮረ በመሆኑ ከግብፅ ጋር የምንከተለው ፖሊሲም ከዚህ የተለየ አይደለም ብለዋል።

ግብፅ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ነገር ከሀገሯ እንደምታወጣ እና ኢትዮጵያም ተመሳሳይ እርምጃ እንደምተወስድ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውንም አስታውቀዋል።

ይህንን መቀመጫቸውን በግብጽ ካይሮ አድርገው በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውን ሁከት ሲመሩ በነበሩ ተቋማት ላይ የሀገሪቱ መንግስት አርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቀዋል።

የአረብ ሀገራት በምስራቅ አፍሪካ አካባቢ የሚያደርጉት እንቅስቃሴም ለኢትዮጵያ አያሰጋም ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሀገራት በር በመሆኗ የአውሮፓም ይሁን የአረብ ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ያላቸው ፍላጎት ከፍተኛ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy