Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

”መወደሰ አባይ” የግዕዝ ቋንቋና የቅኔ ምሽት በባህር ዳር ከተማ ተካሄደ

0 1,183

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ባህር ዳር  መጋቢት 26/2009  የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በግዕዝ ቋንቋ የተፃፉ ቀደምት የምርምር፣ የሳይንስና የኪነጥበብ መፅሃፍትን በማስተርጎም ለመማር ማስተማር ስራ ለማዋል እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን ስድስተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ”መወደሰ አባይ” የግዕዝ ቋንቋና የቅኔ ምሽት በሙሉዓለም የባህል ማዕከል ትናንት ተካሄዷል።

በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የአባይ፣ ባህልና ልማት ጥናትና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉቀን አንዱዓለም በፕሮግራሙ ላይ እንደገለፁት የግዕዝ ቋንቋን ህዳሴ ለማምጣት ዩኒቨርሲቲው በመስራት ላይ ነው።

በአክሱም ዘመነ መንግስት ወቅት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የነበረው የቋንቋው ተናጋሪዎች ቁጥር በአሁኑ ወቅት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብቻ ተወስኖ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም ከ13ኛው  ክፍለ ዘመን ጀምሮ የሚገኙ የ78 ነገስታት መዋለ ዜናዎችን ፣ ታሪኮችን፣ ሳይንስ፣ ፍልስፍናዎችን የሚያትቱ መጽሃፍትን ከያሉበት በመሰብሰብ ወደ አማረኛ ቋንቋ በማስተርጎም ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ የትርጉም ስራው እየተከናወነ ሲሆን እስካሁንም የአብዛኞቹ መፃህፍት ትርጉም ስራ መጠናቀቁንና በቅርቡም ተጠርዞ ጥቅም ላይ እንደሚውል አብራርተዋል።

በዩኒቨርስቲው የግዕዝ ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት መስክ ሆኖ እንዲሰጥም የካሪክለም ቀረፃ መካሄዱንና የገበያ አዋጭነት ጥናት መካሄዱን አብራርተዋል።

የባህር ዳር ሃገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት ሰባኪያነ ወንጌል ማህበር ሰብሳቢ ሊቀ ብርሃናት አመሃ ስላሴ አይነኩሉ በበኩላቸው  ”መወደሰ አባይ” የግዕዝ ቋንቋና የቅኔ ምሽቱ በታሪካዊው ቋንቋ ዓባይን የሚያወድስ ቅኔ በመዝረፍ  ለግድቡ ግንባታ ተሳትፎውን እንዲያጠናክር ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ቋንቋውን ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ በየአብያተ ክርስቲያናት በተቋቋሙ መደበኛ ትምህርት ቤቶች የግዕዝ ቋንቋ እንደ አንድ ትምህርት በመደበኛነት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።

የሙሉዓለም የባህል ማዕከል ስራ አስኪያጅ አቶ ምስራቅ ተፈራ በበኩላቸው ”መወደስ አባይ” የግዕዝ ቋንቋና የቅኔ ምሽት የታላቁን የህዳሴ ግድብ ታሪካዊነት በታሪካዊው የግዝ ቋንቋ ለወጣቱ ትውልድ ለማሳወቅ ያለመ ነው።

ሀጋራዊ እውቀትን በመጠቀም ህብረተሰቡ ለህዳሴው ግድብ የሚደረገውን ድጋፍ አጠናከሮ እንዲቀጥል ለማድረግ እንደሆነም ተናግረዋል።

”መወደሰ አባይ” የግዕዝና የቅኔ ምሽት የተለያዩ ምሁራን ቋንቋው አሁን ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን አባይን የሚያወድስ በቋንቋው ቅኔ ሲዘረፍ አምሽቷል።

የሙሉዓለም የባህል ማእከል ከባህር ዳር ሃገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት ሰባክያነ ወንጌል ማህበር ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ የሃይማኖት አባቶች የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ምሁራን፣ ወጣቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy