NEWS

ምክር ቤቱ በአንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን ሁከት አስመልክቶ የቀረበውን ሪፖርት አጸደቀ

By Admin

April 20, 2017

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያ እና አማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች እንዲሁም በደቡብ ክልል ጌዲኦ ዞን የተከሰተውን ግጭት አስመልክቶ ያቀረበውን ሪፖርት አጸደቀ።

ምክር ቤቱ በየደረጃው ባሉ የመንግስት አካላትና ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ በወሰዱ የፀጥታ ሃይሎች ላይ ማጣራት ተደርጎ ለህግ እንዲቀርቡ በኮሚሽኑ የተሰጠውን ምክረ ሃሳብም ደግፏል፡፡

በብሄር ተኮር ጥቃት ከአካባቢያቸዉ የተፈናቀሉ ዜጎችም በአፋጣኝ ይቋቋሙ ብሏል ምክር ቤቱ።

ከዚህ ባለፈም በጌዲኦ ዞን ብሄርን መሰረት ባደረገ ጥቃት ላይ ተሳትፎ ያደረጉ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የጸጥታ አካላት እና የጌዲኦ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እንዲጠየቁም ወስኗል።

በተመሳሳይ በባህርዳር በነበረዉ ሁከት ተሳትፎ ያደረገው የሰማያዊ ፓርቲ እና በኦሮሚያ ለተፈጠረው ቀውሰ የአባባሽ ሚና የተጫወተው የአሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፊኮ) አባላት ይጠየቁ ሲልም ውሳኔ አሳልፏል።