Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሥርዓቱ በህዝቦች ሉዓላዊ መብቶች ላይ ድርድር አያውቅም!

0 304

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሥርዓቱ በህዝቦች ሉዓላዊ መብቶች ላይ ድርድር አያውቅም!   /ዳዊት ምትኩ/

ዛሬ ኢትዮጵያ በምትከተለው ፌዴራላዊ ሥርዓት አያሌ ድሎችን ማስመዝገብ ችላለች፡፡ ሕዝቦቿም የውጤቶቹ ተቋዳሽ ለመሆን በቅተዋል፡፡ ይሁንና የቀድሞው ሥርዓት ተመልሶ ይመጣ ዘንድ ጨለምተኞቹ ሠላሙን አግኝቶ ኑሮውን ለመለወጥ የሚጣጣረውን ዜጋ ወደ ኋላ ለመጎተት የማይቀበጣጥሩት የለም፡፡

አስተማማኝነቱን በተግባር በማረጋገጥ ላይ የሚገኘውን ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በማጥቆር ሥራ የተጠመዱት እነዚህ ፅንፈኛ ኃይሎች የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን እድገትና አንድነት ሠላም ነስቷቸው የማይወረውሩት የአሉባልታ ድንጋይ የለም።

ህገ መንግሥቱ ፀድቆ በሀገሪቱ የፌዴራል ሥርዓት እውን ከሆነ ወዲህ የሠላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ጉዳዮች ምላሽ እያገኙ መምጣታቸው ይታወቃል፡፡ ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር፣ የሚፈልጉትን ኃይማኖት የመከተል፣ በቋንቋቸው የመናገር እና የመጻፍ፣ ባህላቸውን እና እሴቶቻቸውን በነጻነት የመግለፅ መብቶቻቸን ህገ መንግሥቱ በማያሻማ መልኩ አረጋገጠላቸው፡፡ በእርግጥም የኢትዮጵያ ህዝቦች የዘመናት ትግል መንስዔም እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ነበርና ነበርና ይህም ሆነ፡፡

ጨለምተኞች የፌዴራሊዝም ሥርዓት በኢትዮጵያ ተግባራዊ ከሆነ ሀገሪቱ ወደማያባራ ጦርነት ውስጥ ትገባለች፤ ሀገሪቱም የመበታተን አደጋ ይገጥማታል፣ ህዝቦቿም በየጎራው ተከፋፍለው እርስ በርሳቸው ይጨራረሳሉ በማለት አሟረቱ፡፡ የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃን ብዙ ደሰኮሩ፤ የፖለቲካ ተንታኞች ብዙ ቀበጣጠሩ፤ ጽንፈኞች ፌዴራላዊ ሥርዓቱ ለሀገሪቱ አይበጅም ሲሉ ብዙ አራገቡ፡፡

ሆኖም የፌዴራሊዝም ሥርዓት በማህበራዊ ምንነት ምክንያት የሚፈጠር ልዩነቶችን ለማቻቻል አብሮ ለመጓዝ ብሎም በማህበራዊ ምንነት ወይም በሌላ የማንነት ልዩነቶችን መሠረት ያደረጉ ግጭቶችን ለማስተንፈስ አግባብነት ያለው የፖለቲካ መሣሪያ መሆኑን የመስኩ ተመራማሪዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ይህ አብሮነትም ዜጎች የጋራ ምጣኔ ሀብታቸውን ለማሳደግ ሥርዓቱ የጎላ ሚና እንደሚጫወትም እምነት ተይዟል፡፡

ይህን እውነታ የተገነዘበው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊው የሀገሪቱ መንግሥትም ህገ መንግሥቱን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በገዛ ፈቃዳቸው ተስማምተው እና ተማምነው እንዲያፀድቁት የተጫውተው ሚና የላቀ ነው፡፡

ኢትዮጵያን ከአምባገነኑ የደርግ ሥርዓት አገዛዝ ያላቀቀው ኢህአዴግ መራሹ ሥልጣን በህዝብ እና በህዝብ ብቻ የሚረጋገጥ እንደሆነ በማመን ዜጎች የትግላቸው ባለቤት እንዲሆኑ አስችሏል፡፡ ህገ መንግሥቱ የህዝቦች የዘመናት ትግል ውጤት ነውና፤ ይህን የህዝቦችን የዘመናት ትግል ግምት ውስጥ በማስገባት ነበር ህገ መንግሥቱም ሊረቀቅና ሥራ ላይ ሊውል የቻለው፡፡

የኢትዮጵያ ባህል፡ ቋንቋ እና ታሪክ ማለት የኢትዮጵያ ህዝቦች ባህሎች፡ ቋንቋዎች እና ታሪኮች ተደምረው የሚፈጥሩት ነው፡፡ ይህ እውነታ በልዩነት የሚስተናገደው በፌዴራሊዝም ሥርዓት ነው፡፡ እናም ለሀገሪቱ ብቸኛው አማራጭ ፌዴራላዊ ሥርዓትን መከተል እንደሆነም አማራጭ የለውም፡፡

አንዳንድ ጨለምተኞችና ፅንፈኞች ሀገሪቱ ባልተረጋጋ ውስጣዊ የፖለቲካ ችግር ትናጋለች፣ ህዝቦቿም እርስ በርሳቸው ይተላለቃሉ የሚሉ እሳቤዎችን ከተቃዋሚ ኃይሎች የእብደት ትንታኔ እየሰጡ ዋትተዋል፡፡ ሆኖም ይህን የሴራ አቋማቸውን ማንም አልተጋራቸውም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ግልጽ ነው፡፡ የፌዴራል ሥርዓቱ ጨለምተኞቹ የሚሉትን ዓይነት በድንቡሽት የተገነባ ቤት ሳይሆን፤ በህዝቦች ፈቃድ ተረጋግጦ በጠንካራ መሠረት ላይ የተገነባ በመሆኑ ነው። እናም ሥርዓቱን የተመለከቱበት መነፅር የተሳሳተና የተገለበጠ ህልም ብቻ የሚያሳያቸው መሆኑ በተግባር ታይቷል፡፡

ታዲያ ይህ እኩይ ተግባራቸውም የሚያመላክተው ነገር፤ ልክ እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም ታሪክ ራሱን በመድገም እነዚህ ኃይሎች የሥርዓቱን እመርታ ቁጭት በተንሸዋረረው  የተገለበጠ መነፅር እየተመለከቱ ለማደናገር መሞከራቸውን ነው። እርግጥ የማምታታትና የማደናገር ሙከራቸው ምንም ውጤት ሊያስገኝላቸው አልቻለም፡፡ መላው የሀገሪቱ ህዝቦች በደማቸው የፃፉት ህገ መንግሥት ፀድቆ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችም በአንድነት ተሳስረው የእድገት ጉዟቸውን ተያይዘውታል፡፡

አላዛኞችም የሚደልቁት የቆርጦ ቀጥልነት አታሞም ሰሚ አጥቷል፡፡ እናም በሚያስገርም ጨለምተኛ እሳቤያቸው ዓለም የመሰከረውንና ዕድገት ያመጣውን ፌዴራላዊ ሥርዓት ከሽፏል ይሉናል፡፡ አንዳንዶቹ ጭራሹኑ በግጦሽ ቦታና በውኃ ምክንያት በአንዳንድ የሀገራችን ብሔረሰቦች መካከል ለዘመናት ሲከሰቱ የኖሩ ግጭቶች መኖራቸውን እንዲሁም አማርኛ ተናጋሪዎች ከአንዳንድ አካባቢዎች ተባረሩ በሚሉ  የፌዴራል ሥርዓቱ በእነዚህ ጉዳዮች ምክንያት ከሽፏል ብለው ይሉናል፡፡ በድፍረትም ፅፈዋል።

በጨለማ ውስጥ ሆነው በገሀዱ ዓለም የሌለን ነባራዊ ሁኔታ እየተነተኑ አፈ ታሪክ ያንበለብሉልናል፡፡ በየትኛውም ማኅበረሰብ ውስጥ ግጭት መቼም ቢሆን ሊጠፋ የማይችል ነባራዊ ሁኔታ መሆኑን እያውቁም ወይም ቢያውቁም ለመናገር የሚደፍሩ አይደሉም። ምክንያቱም ለእነርሱ ጥላሸት የመቀባት ሥራ ይህ ሀቅ ምንም ስለማይጠቅማቸው ነው።

ሆኖም እንኳንስ የህዝቦች ንቃተ ህሊና እየተገነባ እና ይበል የሚያሰኝ ደረጃ ላይ እየደረሰ ባለበት በእኛ ሀገር ውስጥ ቀርቶ በሥልጣኔ በበለፀጉ ሌሎች ሀገሮች ውስጥም ቢሆን ግጭት መኖሩ አይቀርም። ምን ይህ ብቻ፡፡ ሰው ከራሱ፣ በአቅራቢያው ካለውና ከተፈጥሮ ጋር መጋጨቱም አይቀሬ ነው።

ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ በዓለማችን ላይ ያለው የተፈጥሮ ሀብት እጥረት ነው። ኢትዮጵያም ከዚህ የተለየች አይደለችም — እንደ ማንኛውም የዓለማችን ክፍል የተፈጥሮ ሀብት እጥረት አለባት። እናም ግጭት ትናንትም ይሁን ዛሬ መኖሩ ያለና የሚኖር ጉዳይ ነው።

ሆኖም ፌዴራላዊ ሥርዓቱ ካለፉት ጊዜያት ጋር ፈፅሞ በማይገናኝ መልኩ ለዚህ ነባራዊ ችግር ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ ሁኔታውን በመለወጥ ላይ ይገኛል። የሀገሪቱ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ያላቸውን የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ እንዲጠቀሙና ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመተሳሰብ የጋራ ሀብታቸው እንዲሆን ማድረግ ችሏል።

ዳሩ ግን ያለፉት ሥርዓቶች በሀገሪቱ ህዝቦች ውስጥ ፈጥረውት ያለፉት የተዛቡ አመለካከቶች እንዲህ በቀላሉ በጥቂት ዓመታት በቀላሉ የሚቀየሩ አይደሉም — ሂደትን፣ ጊዜንና የአስተሳሰብ ለውጥን ይጠይቃሉ። አንዳንዶች ይህን እውነታ ወደ ጎን ገሸሽ አድርገው ሥርዓቱን ጥላሸት ለመቀባት ካላቸው ፍላጎት ብቻ በመነሳት ‘የከሸፈ ፌዴራሊዝም’ መሆኑን ያለ አንዳች ሐፍረት ሊነግሩን ሞክረዋል። ይህ ደግሞ የለየለት ውሸት መሆኑ ተረጋግጧል። እንደ ሟርተኞቹ እሳቤ ሳይሆን የፌዴራል ሥርዓቱ በእርግጥም አልከሸፈም። ይልቁንም ሥርዓቱ የሀገሪቱን ህዝቦች በአንድነት በማስተሳሰር ከሰሃራ በታች ጠንካራ ምጣኔ ሃብት መገንባት የቻለና ህዝቡንም በየደረጃው ተጠቃሚ ያደረገ ሆኗል። ስለሆነም ‘የክሽፈት ዓለም’ ምኞት በጨለምተኞቹና በጽንፈኞቹ ምናብ ውስጥ እንጂ በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ውስጥ የሌለ መሆኑን ማሳወቅ ተገቢ ይሆናል።

ግራ ተጋብተው ሌሎችን ግራ ለማጋባት የሚውተረተሩ ጥቁር ቀለም ቀቢዎች ሸውራራ ሀሳብ ጠቅለል ተብሎ ሲታይ፤ ገዥው ፓርቲ የብሔር ብሔረሰቦችን ሉዓላዊ መብት ለፖለቲካ ፍጆታ እየተጠቀመበት እንደሆነ በተለመደው ‘እገሌ የተባለ ሰው እንዲህ ስላለ ትክክል ነው’ በሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ሊሞግቱ ይዳዳቸዋል፡፡

ይህን የለየለት ውሸት በሚገባ ለሚገነዘብ በጉዳዩ ላይ ብዙ ማለት ተገቢ አይደለም። ይሁንና እዚህ ላይ አንድ ሀቅን ማንሳት ተገቢ ይሆናል፡፡ ገዥው ፓርቲ የታገለለትንና በህገ መንግሥቱ ውስጥ ተካትቶ ዛሬም ሆነ ነገ በፅናት የሚያምንበትን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የማይገሰሱ መብቶች ላይ ከቶም ቢሆን ድርድር እንደማያውቅ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ መደራደር

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy