Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሲኖትራክ በባቡር መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት አደረሰ

0 1,772

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሲኖትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ሳሪስ አዲስ ጎማ አካባቢ በባቡር መሰረተ ልማት ላይ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት አደረሰ።

አደጋው በሰው ህይወት ላይ ጉዳት አለማድረሱን የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢዜአ ገልጸዋል።

ነገር ግን 500 ሺህ ብር ግምት ያለው የባቡር መሰረተ ልማት መውደሙን ነው የተናገሩት።

አደጋውን ያደረሰውን ተሽከርካሪ በክሬን ከሀዲዱ ላይ የማንሳት ስራ መከናወኑንና 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት ማዳን እንደተቻለም አስታውቀዋል።

የጭነት ተሽከርካሪው አደጋውን ያደረሰው ትናንት ከሌሊቱ 8፡00 ሠዓት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አዲስ ጎማ ፊት ለፊት በሚገኘው የባቡር መሰረተ ልማት ላይ ነው።

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት አደጋው የባቡር አገልግሎቱን ለሶስት ሠዓታት እንዳስተጓጎለው ገልጿል።

የአገልግሎቱ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አወቀ ሙሉ ተሽከርካሪዎች በተደጋጋሚ የሚያደርሱት አደጋ ድርጅቱ ለደንበኞቹ በሠዓቱ አገልግሎት እንዳይሰጥ እንቅፋት እየሆነ ነው ብለዋል።

የጭነት ተሽከርካሪው ከሃዲዱ ላይ እስኪነሳ የመስመሩ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ በመቋረጡ በድርጅቱ ላይ ከሚደርሰው ኪሳራ ባሻገር ደንበኞቹ መጉላላታቸውን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ምክትል ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ እንደገለጹት ኮድ ሶስት 53989 የሆነው ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ከፍጥነት በላይ በማሽከርከር በባቡር መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት አድርሷል ብለዋል።

አሽከርካሪው ከጎተራ ወደ አቃቂ አቅጣጫ ሲያሽከረክር የሚያስጠነቅቁ የትራፊክ ምልክቶችን በማለፍ በባቡር ሀዲዱ ማቋረጫ ላይ ጉዳት ማድረሱን አስረድተዋል።

በወቅቱ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በአካባቢው የመንገድ ጥገና እያካሄደ ቢሆንም በቂ የትራፊክ ምልክቶች እንደነበሩም ገልጸዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy