Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሲዊዘርላንድ በስደተኞች ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መሥራት እንደምትፈልግ ገለፀች

0 420

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሲዊዘርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር በስደተኞች ጉዳይ ላይ በትብብር መሥራት እንደምትፈልግ የአገሪቷ የስደተኞች ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ማሪዮ ጋቲከር ገለጹ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ የስደተኞች ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋቲከርን በጽህፈት ቤታቸው ዛሬ ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ጋቲከር እንደተናገሩት፥ በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ የስደተኞች ጉዳይ አሳሳቢ ችግር በመሆኑ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል።

በዚህም ሲዊዘርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር በስደተኞች ዙሪያ በትብብር የመሥራት ፍላጎት እንዳላት ነው የገለጹት።

ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን፣ የሶማሊያ እንዲሁም የኤርትራ ስደተኞችን ተቀብላ ማስተናገድ መቻሏን አገራቸው በአድናቆት እንደምትመለከተውም ተናግረዋል።

ውይይቱን የተከታተሉት የአውሮፓ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ፥ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ታሪካዊና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል።

በዚህም መሰረት ሲዊዘርላንድ በስደተኞች ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ከቁሳቁስ ድጋፍ ጋር እያቀረበች መሆኑን ጠቁመዋል።

ሁለቱ አገሮች ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል ምክክር በጥቅምት 2010 ዓ.ም ላይ ያካሂዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው ያነሱት።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከ800 ሺህ በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ተቀብላ እያስተናገደች ነው።

ሲዊዘርላንድ ኤንባሲዋን በአዲሰ አበባ የከፈተችው እ.ኤ.አ በ1962 መሆኑን ኢዜአ በዘገባው አስታውሷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy